Hiber Radio Daily Ethiopia News January 17, 2023
በካሊፎርንያ እጅግ ሰፊ መሬት ለገዳም ምሥረታ ተቀብለናል። መሬት ወርቅ በኾነባት ዱባይ እጅግ ሰፊ መሬት ለቤተ መቅደስ ግንባታ ተረክበናል። በአውሮፓም ገዳም ለመመሥረት ላይ ታች እያልን ነው።
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በየሔደችበት ስፍራ የሚሰጣት በጸጋ የታተመች ልዩ እመቤት ናት። ይህ ደግሞ በዘመነ ኦሪት የተጀመረ መኾኑ በጣም ይደንቃል። ማንም የውጭ ሀገር በምድረ እስራኤል ስፍራ ሳይኖረው ዴር ሡልጣንን የሚያኽል መሬት የተቀበልን እኛ ብቻ ነን።
በየሔድንበት ቦታ ይለካልናል። ለምን? እግዚአብሔር የሚፈልግብን አገልግሎት ስላለ ነው። ተጎራብተናቸው የምንኖራቸው ወደ በጉ ሠርግ ያልጠራናቸው ብዙ ናቸው። ዛሬ በብዙ የዓለማችን አፍዛዣዎች ብዙ አብያተ መቅደስ አቋቁመናል። በየሔድንባቸው የሚኖሩትን ሕዝቦች ግን ተጎራበትናቸው እንጅ አላመጣናቸውም።
አቡነ ይስሐቅ የሚባሉ ኮከብ ብልጭ ብለው ተሰወሩብን። እጅግ ታላቅ ታሪካዊ ሐዋርያዊ ሥራ ሠርተዋል። በካሪቢያን፣ በአሜሪካ እና ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሽ ሐዋርያዊነት ፈጽመዋል። ወደ ሐዋርያዊው ቅዱስ ባኮስ እና ወደ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ሥራ መሔድ አለብን።