The Council of Ministers has passed decision to open up the banking sector to foreign investors today, the Office of the Prime Minister said.. Opening up the banking industry to foreign investors supports the sector’s services with knowledge and technology and move the country’s economy to a higher level of connection with the international market, the statement noted.
The policy will also help to increase competitiveness and efficiency of the financial sector, to have sufficient financial supply, to facilitate the supply of foreign currency, to increase job opportunities, and to ensure continuous economic growth by ensuring economic efficiency and global competitiveness, the council observed.
Therefore, the Council of Ministers has extensively discussed, enriched, and passed the draft policy to be implemented.
ENA
በጓሮ በር
ተጠምዛዡ ጠምዛዥ
አጎብዳጁ አስጎብዳጅ
አዋጅ ሲያወጡበት እያወጣ አዋጅ
አንጡራውን ሁሉ ካየር እስከ ባጃጅ
ሸጦ ሊጨርስ ነው ሊያስይዘን በአጋጅ
ኧረ ጉድ በል ጦቢያ!
አድዋ ላይ ያስቀሩት ያ ባርነት መጣ ገባ በጓሮ በር
የእያንዳንድህ ጥሪት ባባእድ ዘራፊ ሙልጭ ሊመዘበር
አሁን ነው ሚጠቅመው የሀገር አንድነት
ባንድ ቼክ ሲጀወር ሁሉም ለባርነት።
ኢትዮጵያ ዝለቁ
አረብና ፈረንጅ የቅርቡ የሩቁ
የምዕራብ ምሥራቁ
አምና በባርያ ንግድ ባንክ የከፈታችሁ ገባ ገባ በሉ
ሰምሯልና ዛሬ ባርያ ክነቀዬው የመግዛት እድሉ
ፊት ለፊት አትምጡ ጦርነቱ ቀልጧል ጦፏል ግርግሩ
በጓሮ ይሻላል በሩን ገርበብ አርጎ ባለበት አሽከሩ።
አጋጅ = ወለድ አግድ የሚይዝ አበዳሪ ባለንዋይ።
የግጥሙ መታሰቢያነት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደተጠፈረ በንዋይ የተጥለቀለቁ የባእዳን ባንኮች ገብተው ከሁለመናው እንዲነቅሉት በብልጽግና ለተወሰነባት የተረገመች ቀን።