Menu
Dark
Light
Today: December 21, 2024

ጋልዋክ ቱት የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

April 17, 2013

(ዘ-ሐበሻ) በጋምቤላ ሕዝብ ስም ለሕወሓት በተላላኪነት እየሠራ የሚገኘው የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ከዚህ ቀደም ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት ያስተዳድሩ የነበሩትን አቶ ኡሞድ ኡቦንግን አሰናብቶ አቶ ጋልዋክ ቱትን ሹመት ማጽደቁን ከሥፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ።
እንደመረጃው ከሆነ የሕወሓት ተላላኪው ምክር ቤቱ ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡቦንግ ለሌላ የሥራ ኃላፊነት በመታጨታቸው (ከዚህ ቀደም ዘ-ሐበሻ አቶ ኡሞድ ኡባንግ እንደሚዘዋወሩ ዘግባ ነበር) ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኃላፊነት ለመነሳት ያቀረቡትን ጥያቄ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ በማጽደቅ በምትካቸው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩትን አቶ ጋልዋክ ቱትን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል። በሌላ በኩልም ኢንጅነር ኡሌሮ ኦፒዮ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
በክልሉ ነዋሪዎች “እውነተኛው ወያኔ” የሚል ስያሜ ያላቸው አቶ ኦሞት፣አቶ መለስ መታሰር አለባቸው በማለት የተናገሩት ከታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚመራ ግምገማ እተካሄደ ባለበት ወቅት ነው።
በአንድ ወቅት “እኔ ከታሰርኩ መለስም ይታሰራል” በማለት በከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት ፊት እንደተናገሩ የተዘገበላቸው ኤቦንግ በጋምቤላ አኝዋኮች ጭፍጨፋ ስም ዝርዝር ጽፈው ሰጥተዋል፣ በክልሉ ያለው መሬት ነጠቃ እንዲስፋፋ አድርገዋል፣ ሙስና እንዲስፋፋና በጋምቤላ ሕዝብ ንብረይ ሕወሓት እንዲያዝበት አድርገዋል በሚል በክፍተኛ ሁኔታ ሲተቹ ቆይተዋል። በተለይም ር ዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በሙስና ተዘርፏል በተባለ 80 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ፣ በብቃት ማነስ፣ ልማትን በማጓተትና በጎሳዎች ዕርስ በርስ ግጭት ሰበብ የተገመገሙት ኦሞድ ኤቦንግ በድንገት ከዛሬ ዘጠኝ ኣመት በፊት ለተካሄደው ጭፍጨፋ ተጠያቂ መደረጋቸው “እኔ ከታሰርኩ ወታደርና መሳሪያ የሰጠኝ አቶ መለስም ይታሰራል” ማለታቸው አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ነበር – በአንድ ወቅት።
ኦሞድ በየትኛው የመንግስት መሥሪያ ቤት እንደተሾሙ ባይታወቅም፤ አዲሱ የሹመት ዝውውር ሆን ብሎ እርሳቸውን ለመምታት በሕወሓት የታሰበ ትልቅ ሴራ የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

The Rulers of Ethiopian Should Face Justice for Crimes They Committed Against Amharas in Ethiopia

Next Story

ESAT SPORT AFCON 2013 SPECIAL FISSEHA WITH METI

Latest from Blog

Assad Flees 1

Post-Assad Syria: Navigating Hope and Uncertainty

Dahilon Yassin The Syrian uprising against Bashar al-Assad’s regime which escalated into a civil war was violently crushed by the Syrian government in 2011. 13 years later, a surprise rebel offensive reached
Go toTop