Voice of Amhara Daily Ethiopian News April 14, 2017

1 min read


Voice of Amhara Daily Ethiopian News April 14, 2017

Read Aloud:   Ethiopian Airlines wins Decade of Airline Excellence Award for Africa region

3 Comments

 1. Avatar of ደምስ የሚባለው በበኩሉ የመኢሶን ገራፊነት ታሪኩን እያነሱ ቀልቡን የሚገፉት እንዳሉ ሲታወቅ ደምስ የሚባለው በበኩሉ የመኢሶን ገራፊነት ታሪኩን እያነሱ ቀልቡን የሚገፉት እንዳሉ ሲታወቅ says:

  ኢትዮጵያዊያንን ድርጅት በማፍረስ ስለሚታወቀው ደምስ በለጠ ታሪክ ባጭሩ (በካሳየ መርሻ — ከጀርመን)

  Posted by: ecadforum March 18, 2017

  በካሳየ መርሻ — ከጀርመን
  ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግምባር ውስጥ በተለያዩ ሰዎች በተለያየ ጊዜ የድርጅቱ አባላት በነበሩ ለጥቅምና ለዝና ሲሉ ገብተው የነበሩ ከብዙ በጥቂቱ ከሰሎሞን ተካልኝ ጀምሮ እስከ አርበኛው የሚሰለጥንበት ማሰልጠኛ ጣቢያ የሚያሳየውን ካርታ ለጠላት አሳልፈው የሰጡትን ለአርበኛው ተብሎ የተሰበሰበውን ገንዘብ የበሉትንና እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ በዚህ በጀርመን አገር በአርበኛው ስም ጥገኝነት ለሚጠይቁ ወገኖቻችን ወረቀት በመሸጥና እህቶቻችንን በማዋረድ ያለ ፍላጎታቸው በግዴታ የምስክር ወረቀት ማግኘት ከፈለግሽ ከኔ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት አርድጊ እያሉ እያስገደዱ እስካሉት ወራዳና ስግብግብ ከሃዲ የቀድሞው የአብዮት ጠባቂ የልደቱ ክህደቱ ኢዲፓ ፓርቲ አባል የነበረውና ቅን ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ እንደሚባለው ቅንጅትን ወክሎ ገብቶ መጨረሻ ቅንጅትን ከድቶ ለሆዱ ሲል ፓርላማ ገብቶ ከነበረው ከሃዲ ድረስ ያለውን በድርጅት ስም ለሀገር ለወገን ሲሉ መተኪያ የሌላት ሕይወታቸውን ሲከፍሉ የነበሩና አሁንም በመክፈል ላይ ያሉትን ብርቅዬ በሀገሪቱ ልጆች ላይ የተፈፀመውን ታሪክ ይቅር የማይለውን ወንጀል ከነ ሙሉ ማስረጃ ጋር በመጽሐፍ መልክ ለወደፊቱ የማቀርበው ቢሆንም አሁንም ባለፈው ወንጀል የማይፀፀተው ምንም እንኳን አገውንና አማራን ፈፅሞ ልንለየው የማንችለው አንድ ሕዝብ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም እኔ አገው እንጅ አማራ አይደለሁም ሲል የነበረ ጎጠኛ ፍጡር አሁን ደግሞ ባዲስ መልክ አማራ ነኝ በሚል የበግ ለምድ ለብሶ ብቅ አለ።Demis Belete
  እንደሚታወቀው ከአራት አመታት በፊት በጉራፋርዳ አማራው ተወልዶ ባደገበት እናት አገሩ እንደ ዱር አራዊት እየታደነ ሲባረርና ሲታረድ በነበረበት ወቅት በመቆርቆር አለሁልህ በሚል ሞረሽ ወገኔ ሲመሰረት በገንዘብ ሁላችን ባንረዳውም አድናቆት የቸርን በርካታ ወገኖች ነበርን።በአባልነትና በደጋፊነት በማህበሩ ውስጥ ሀገር ወዳድና ቅን ወገኖቻችን ሲሳተፉ እንደነበር ይታወቃል። እንደሚታወቀው በሀገራችን በትግሉ ሂደት ያጋጠሙን ችግሮችና እጥረቶች የመገናኛ ተደራሽነት አለመኖርና የራዲዮኖቻችን ቁጥር ማነስበ ሳይሆን ወይም ነፃ መውጣት ያለበት መከራ ቀማሹ ዘሩ እየጠፋ ያለው ወገናችን የትግሬ ወራሪን ምንነት የማያውቀው ስለሆነ ይህን የሚነግረው በማጣቱ ሳይሆን በቅንነት አብሮት ከአጠገቡ ሆኖ የሚሞትና የሚደማ የሚያስትጥቀው ታግሎ የሚያታግለው ቆራጥ የክፉ ቀን ወገን ማጣቱ ብቻ ነው። መጠቆም ወደፈለኩት ጉዳይ ስመለስ ሞረሽ ለምን ራዲዮ ከፈተ ሳይሆን ማነው በኤርትራ መንግስት የሚደገፈውን አርበኞች ግንቦት7ን የሚጠላና በቆርጥነት ሊዘምትበት የሚችል ሰው ተብሎ በባትሪ ሲፈለግ ምንም እንኳን አገውንና አማራን የማንለየው አንድ ሕዝብ ቢሆንም ትላንትና እኔ አገው እንጅ አማራ አይደለሁም ሲል የነበረን ጎጠኛ በትላንትናው ወንጀሉ የማይፀፀተውን ፍጡር ደምስ በለጠን አገኘ። ይህ ሰው እንደፈለገ ከመቀራረብ ይልቅ ጥላቻን እንዲሰክብ ሁሉም በጋራ እንዳይነሳ መከፋፈል መኖሩን ለሕዝባችን መርዶ የሚነግር መልዕክት እንዲያስተላልፍ ፈቃድ መሰጠቱ ነው።
  ይህ ጎጅ መልዕክት የአባላቱ ፍላጎት ይሆን? መልሱን ለነሱ እተወዋለሁ። በድርጅቱ ስም የሚወጡት መግለጫዎችም ያተኮሩት በወያኔ ላይ ሳይሆን በሚሰሩ ድርጅቶች ላይ ሆኖዋል። ከቶ ለማን ጥቅም ይሆን? እኔ እንደሚገባኝ ከሆነ ከሌሎች ስብስቦችምጋርም ሆነ ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር አብሮ ለመስራት ችግራቸው ከሞረሽ ወገኔ ከማህበሩ ጋር አይመስለኝም። እኔ በበኩሌ የሞረሽ ወገኔ ወንድሞቼን የምማፀነው ቢቻል ከሌሎች ጋር አብሮ ተግባብቶ መስራት እንዲቻል መጣር። ካልሆነ ደግሞ በትግሬ ወራሪ ላይ የራሳቸውን አስተዋፅኦ እያደረጉ ባሉ ድርጅቶች ላይ ከመዝመት ይልቅ ድምጽን አጥፍቶ መስራትን ብቻ የሚጠይቅ ትግል በመሆኑ በጉዳጉ ተወያይቶ በቶሎ መፍትሄ ፈልጎ ማግኘትና ውሳኔ መስጠት ያሰፍልጋል።አነሰም በዛም በቅርቡ ከተመሰረተው አገራዊ ንቅናቄ ጋርም አብሮ ለመስራት ያልጀመረው ከማህበሩ መሰረታዊ 1 አላማዎች ጋር ስለማይጣጣም ብቻ እንደማይሆን ባለተስፋ ነኝ።ወይንስ በማንኛውም ስብስብ ውስጥ ያለን ወገኖች ተፈጥሮ ባደለን መጥፎ የግል ባህሪያችን በሚፈጥረው ቀውስ ነው? ይህ መፍትሄ ማግኘት ያለበት የጋራ ችግራችን ነው። በዚህ አጋጣሚም አገራዊ ንቅናቄውም ለሚቀርቡለት አሳትፉን ጥያቄዎች በጎ ምላሽ የሚያሻው ጉዳይ ስለሆነ በትህትና እጠይቃለሁ። ሁሉንም ለነገ እያልን የምንተዋቸው ችግሮች ሁሉ ከማደግ በስተቀር እንደ ምንፈልጋቸው ራሳቸው አይከስሙም።ወደ ሞረሽ ወገኔ እንደገና ልመለስ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ሁላችንም እንደማያመን ተደርጎ የሚነገር ነገርም ይሰማል። በበኩሌ እኔ የጎንደር ተወላጅ አማራ ነኝ። ህኖም በዚህ እየተደረጉ ባሉ የጥላቻ መግለጫዎች እንዴት ነው ሌላው መሳተፍ የሚችለው?በአገር አቀፍ ደረጃ በተደራጁ ድርጅቶች ውስጥ የታቀፉትን አማራዎች ሁሉ ጭፍን ተከታዮች እየተባለ የሚኮነነዉም ኩነና ማህበሩን ተጨማሪ አባልና ደጋፊ ከማስግኘት ይልቅ ባዶ እንዳያስቀረው ስጋት ያላቸው ሰዎች አሉ።ባህላችንም መሰዳደብና አማራው ጠላቱ ሁሉም እንደሆነ አድርጎ መፈረጅም ጉዳት አለው። ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ይመስለኛል።በዚህ ማህበር ውስጥ ቅን ወገኖች አላችሁና በጋራ ሊሰራ እንዲችል ራሳችንን ጠልፈን እየጣልን ስለሆን ችግሩ የታወቀ ነው መፍትሄም የሚመጣው መነጋገር ሲቻል ነው። የሚጮኸውን ጅራፍ ማስቆም የሚቻለውና እንክርዳዱን የነ ገዱ አንዳርጋቸውንና የነበረከትን ሰርጎ ገቦችን ለይተን የምናውቅበት መንገድ ቀደም ሲል ለአማራው ሕዝብ በተግባር ተቆርቁዋሪነቱን ያሳየው ሞረሽ ወገኔ ብቻ በመሆኑ በአማራ ስም እየተነገደበትና የአማራ መንግስት እንደነበርና አሁንም የአማራ መንግስትና የአማራ አገር እንመሰርታሉት ውነት አማራውን ለመጥቀም ነው?የትግሬን ወራሪ ለማፍረስ ወይንስ ለማጠናከር? ሞረሽ ወገኔ እንዴትስ ዝም ይላል የምትደግፉት አላማ ነው?ደምስ የሚያስተላልፈውንና የሚሰድበውን የስድብ ናዳ ስለሚደግፉላቸውና አጫፋሪ ስላገኛችሁ? እኔ ለሁላችንም አይጠቅመንም ባይ ነኝ። እንደ መብት ባይቆጠርም በግል መሳደብ ይቻላል። እንደሚታወቀው አብዛኛው አማራ ነኝ እያለ የሚጮሆው ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ የትግሬን ወራሪ በጥይት ተራ በትራ ካቆላለፋቸው በሁላ የተፈጠረ ወረርሽ ነው። ይህ ባይፈጠር ኖሮ ይህን ሁሉ ጫጫታ አንሰማው ነበር።
  ትክክለኞቹ ተቆርቁዋሪ የአማራ ልጆች እየጠየቁ ያሉት ደግሞ አሳትፉን በጋራ ጠላታችን ላይ አብረን በጋራ እንዝመት የሚል ነው። በአማራው ስም የተሰገሰገውን ሁሉ ለይቶ ለማወቅ የሌቦችን መደበቂያ ዋሻ ባዶ የምናደርገውም ካሁን በፊት በተግባር እንዴት እንደታየ ልጥቀስ ባለፉት አስር አመታት ሁሉም በየቦታው ጦር አለኝ ሲል በነበረበት ወቅት ምንጊዜም የማልረስው ስውይድን አገር ያለ ድል በአንድነት የሚባል ማህበር ብዙ ወጭ አውጥቶ ድርጅቶችን ለማዋሃድ ፈልጎ በራሱ ወጭ ስቶኮልም ድረስ ጋብዞ አመጣቸው።የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ተመለከተ። ተመሳሳይ ነው ።አገራቸውም አንዲት ኢትዮጵ እንደሆነች ጠላታቸውም አንድ የትግሬው ወራሪ ብቻ መሆኑን አመኑበት። ለመዋሃድም ተስማሙ የመዋሃጃ ቦታው እንዲመረጥም ተስማሙ። ቦታው ታንዛኒያ እንደሆነ አዋሃጁ ማህበር ለሁሉም አሳወቀ። ቀኑ ሲደርስ ውነተኖቹ በቦታው እሲገኙ ምንም ጦር ያልነበራቸው ለሕይወታችን ስለሚያሰጋን ቦታው አውሮፓ ካልሆነ ብለው በቦታው ሳይገኙ ቀሩ። ሌሎቹም የተለያየ ምክንያት ፈጥረው በቦታው ሳይገኙ ቀሩ።ስብሰባው ፓሪስ ይሁንልን አፍሪካ ውስጥ መሄድ ለሕይወታችን ያሰጋናል ያሉት ደግሞ በቦታውም አልተገኙም በዚያው የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩ። ውነተኞቹ እነ መቶ አለቃ ሞላ አባተ በቦታው ተግኝተው ውህደቱን እንደፈፀሙ ወዲያዉኑ ለትግል ጋምቤላ ገቡ። ምክንያት ፈጥረው ያልተገኙት ዛሬ የሌላቸውን ጦር ጦራችንን ይዘን የወያኔን ሕገ መንግስት ተቀብለን ገብተናል ያሉት አቶ ቱዋት ፖል ጋምቤላ ለጋምቤላዎች ብቻ በማለት እንደ ወራሪ ትግሬዎች ትግራይ ለትግሬዎች ብቻ ብለው ኢሕአፓን ከትግራይ እንዳስወጡታና እንደደመሰሱት ሁሉ መቶ አለቃ ሞላ አባተንና ጌታቸው ይስማን በዚህ አትንቀሳቀሱም በማለት በሕዝብ ዘንድ ትልቅ አመኔታ የነበረው ሰው አቶ ቱዋት ፖል አስገደላቸው።በውነቱ ጀግናው መቶ አለቃ ሞላ አባተ በአዕምሮችን የማይጠፋ ኢትዮጵያዊ ነው።እንዴት እንደሞተ ማን እንደገደለው ሲሰጡ የነበሩ መላ ምቶችም ሁሉ ፍፁም ሀሰት ነበር። በዚህ ወቅት እንዳንሳው የተገደድኩበት ምክንያት ደግሞ በወቅቱ መቶ አለቃ ሞላ አባተ ሕይወቱ እንዳለፈች ጌታቸው ይስፋም ቆስሎ በማጣጣር ላይ እንዳለ በስልክ እኔና በከፍተኛ ደረጃ ሲረዳቸው የነበረው ለጊዜው ስሙን መጥቀሱ ስለማያስፈልግ አልፈዋለሁ አግኝተን እነጋግረነዋል። ይህን ሚስጥር 2 ከብዙ አመታ በሁላ ያውጣሁበት ምክንያት ከላይ እንዳልኩት ጥሬው ከግርዱ መለየት ስላለበት የተደረጉትን መፍትሄዎች ለመጠቆም ከማሰብ ነው።የነገዱ አንዳርጋቸውንና የነበረከትን አማራዎች የምንለይበት መንገድ አንዱ ይህ መሆኑንም ለመጠቆም ነው።እንደሚገባኝ በድርጅቶት ላይ ድርጅት የሚመሰረተው ሌላ ችግር ለመድገም ሳይሆን ካሁን በፊት የተፈጠሩትን ላለመድገም ሕዝብን ተስፋ ላለማስቆረጥም ነው ብየ አምን ነበር። አሁን እየተደረገ ያለው ግን በተቃራኒ ነው። ቂም ለመበቀል እኔስ ከማን አንሳለሁ ነው። በፌስ ቡክ በራዲዮ የምትደረገውን ስድብ ሁሉ አገር ቤት ያለው ወገናችን አታመልጠውም ያዝናል ይተክዛል ደሙ ይፈሳል ወራሪው ትግሬ ባልተወለደ አንጀቱ በየደቂቃው ቁምስቅሉን ያሳየዋል ከዚህ በላይ ብዙ ማለት ኣይጠብቅብኝም። ሌላ ምሳሌ ልጨምር አንዲት ሴት ወይም ወንድ ሽንኩርት ስትከትፍ ወይም ሲከትፍ ጣቱ ቢቆረጥ የሚሰማውና የሚሳማት እጃቸው እሱና እሱዋ እንጅ ምሳ ለመብላት ተጋብዞ የሄደው ቁጭ ብሎ እየተመለከተ ያለው ሰው አይደለም። እንዴት እንድሚያም የሚሰማው ደሙ እየፈሰሰ ያለው ባለጣቱ ብቻ ነው። የኛም ፖለቲከኞች የማይሰማቸውና መደሳደም የሚቀናቸው ርህራሄ የሌላቸው የነሱ ደም ስለማይፈስ ብቻ ነው።
  ማተኮር ወደ የሚፈልገው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ለማፍረስ የተካሄደው ሴራ በየተራና በየደረጃው በርከት ባሉ ምንደኞች ስለሆነ በዚህ በደምስ በለጠ ፋይል አቶ ኤልያስ ክፍሌ ብቻ እስከመጨረሻው አብሮ የሚጠቀስ አሳዛኝና ጉልህ ታሪክ ያለው ሲሆን የሌሎቹ ታሪክ በሚቀጥለው ምዕራፍ ጊዜውን ጠብቆ ይወጣልና አሁን የማቀርበው ደረጃ በደረጃ ማስረጃ ያለው ተጨባጭ ታሪክ በአይን የሚታይ የቪዲዮ የአውዲዮ የፅሁፍ በሕይወት ያሉ የበርካታ ሐቀኛ የሰው ምስክሮች የታጀበ ውነታ ነው።እኔ በቀጣይነት በተደጋጋሚ የምጠቅሳቸው ወንድሞቼን በሀገርና በሕዝብ ላይ የሰሩትን መጥፎ በደል በማስረጃ ሳቀርብ የዛሬውን አያርገውና በደህናው ቀን በወቅቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግምባር የሰሩትንም በጎ ነገር ሁሉ በፍፁም አይረሳውም። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ከስለሞን ተካልኝ ጀምሮ እስክ አርበኛው የሚሰለጥንበትን ቦታና ለአርበኛው ተብሎ የተዋጣውን የሕዝብ ገንዘብ የበሉትን ከሃዲዎች ሁሉ ሽንጣቸውን ገትረው የተከራክሩ የተጣሉ ገንዘባቸዉንም ያፈሰሱ በአርበኞቹ ምክንያት በትዳራቸው እክል የገጠማቸው ሰዎች እንደነበሩ እመሰክራለሁ ።በተለይ አንድ እንግሊዝ አገር የሚኖር ወንድማችን አቶ ስለሽ ጥላሁን የነበረውን ፍቅርና የመስራት ፍላጎቱን በፍፁም አልረሳውም። አቶ ኤልያስ ክፍሌም ሆነ አቶ ደምስ ያበረከቱትን ውለታና የደረሰባቸውን ሁሉ በበኩሌ አልረሳውም። በጣም የማከብራቸው ሰዎችም ነበሩ። ሁሉም አርበኛውን ምክንያት በማድረግ በኤርትራ ላይ በጣም ጠንካራ እምነት እንደነበራቸውና የኤርትራ ዜጎች ናቸው ይባሉም እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ የኤርትራውን ፕሬዝደንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂን ቤተመንግስት ድረስ በመግባት ቃለመጠይቅ እንዳደረጉም የሚታወቅ ነው። ባልሳሳት በአመቱ ይመስለኛል ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂን ያመቱ ምርጥ ሰው ተብለው መሰየማቸውም የሚታወስ ነው።
  እነ አቶ ደምስንና ኤልያስ ክፍሌ በወቅቱ በኤርትራ መንግስት ላይ የነበራቸውን የጋለ ፍቅር የተገነዘበ ሁሉ የኤርትራ ዘር አላቸው የሚል ሓሜትም ነበር። እኔንም ያሳመነበት ወቅት ነበር። እኤአ 2010ማርች የመጀመሪያው ሳምንት በመላው ዓለም ተከፋፍለው የነበሩትን የድርጅቱን አባላት በአንድ ማእከል ስር ለማሰባሰብ ታስቦ የተጠራ አንድ ጉባኤ ነበር።ለመጀመሪያ ጊዜ እነ አቶ ደምስንና እቶ ኤልያስ ክፍሌን በአካል የተዋወኩትም ያን ጊዜ ነበር። አብዛኛው ጉባኤ ከመጀመሩ በፊት አስመራ ከተማ የሚደርሰው በተለያየ ቀን ስለሆነና ሁሉም በአንድ ላይ በሰላም እስከሚገባ ድረስ መጠበቅ ስላለ በርከት ላሉ ቀናት አስመራ ከተማ መሰንበት የግድ ይላል። በዚያ ወቅት በኤርትራ መንግስት ወጭ ለኛ ከቦታ ወደ ቦታ የምንዘዋወርበት አውቶቡስ ሲመደብለን እነ አቶ ኤልያስና አቶ ደምስ እንደቤት ልጆች በተለየ መልኩ አንዲት ቀይ ቀለም ያላት የቤት መኪና ተፈቅዶላቸው ያለ ይለፍ እንደፈለጉ በየቦታው ሲፈነጩና ሲዘዋወሩ ስመለከት እንዴ ይሄ ነገር ውነት ነው? እንደሚባለው የኤርትራ ዘር አለባቸው ማለት ነው የሚል ጥያቄ እንድጠይቅ አስገድዶኝም ነበር። እስከዚህ ድረስ ነበር ኤርትራ ውስጥ የነበራቸው መብትና ከነ ኮሎኔል ፍፀም ጋር የነበራቸው ፍቅርና እምነት የተለየ ነበር። ዋናው ታላቁ ሚስጥር ሕዝባችን እየጠየቀ ያለው 3 ጥያቄ መመለስ ይኖርበታል። ታዲያ ከቶ ለምን ይሆን በአንድ ጀምበር የተገለበጡበት ምክንያት ይታወቅ የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ማርች መጀመሪያ 2010 ላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ቀን ደርሶ አርበኛው በአካል የተገኘበት አራት ቀን የፈጀው ጉባኤ ተጀመረ። በዚህ የመጀመሪው ቀን ገና ጉባኤው እንደተጀመረ ከአርበኛው በአዳራሹ ውስጥ የተወሰኑ አርበኞች እጃቸውን በማውጣት ይህ ጉባኤ የአባላት ነው። እነ እቶ ደምስን ስማቸውን በመጥራትና በእጃቸው በመጠቆም እነዚህ ሶስት ሰዎች አጥፊዎቻችን እንጅ አልሚዎቻችን አይደሉም። እንዴት በጉባኤችን ውስጥ እንደ አባል ይሳተፋሉ? የሚል ጥያቄ ተነሳ አርበኛው ሁሉ በአንድ ድምፅ አደራሹን ቀውጢ አደረገው። በዚያ ወቅት በሁኔታው እንኩዋን እነሱ እኛም ደነገጥን ። በጉባኤው የታደሙ የኤርትራ ባለስልጣናት ተጋብዘው በአካል በቦታው ስለነበሩ ሁኔታውን ለማብረድ ሲሉ ሽምግልና ገቡ። አነ አቶ ኤልያስ ክፍሌም ተነስተው ካሁን በፊት የሰሩትን ስህተት ላለመድገምና ለወደፊቱም ድርጅቱን በሙያቸው በቅንነት ሊገለግሉ በወቅቱ ቆመው አርበኛውን ይቅርታ ጠይቀው ተቀመጡ። ጉባኤውም በሰላም ቀጠለ።በመሰረቱ ይህ ሁሉ ሲፈፀም በያንዳንዳቸው አእምሮ ውስጥ ምን ሊቀረፅ እንደሚችል መገመት ይቻላል። ልብ በሉ ይህ ሁሉ ሲሆን በቪዲዮ እየተቀረፀ ነው መለወጥ መካድ አይቻል።በወቅቱ ይህ ጉባኤ እንደተጠናቀቀ ከውጭ የሄድነው አባላት በነፃነት አስራ ሰባት አባላት ያሉት ማእከላዊ ኮሚቴ ስንመሰርት እዚያው ኤርትራ ያለው ዋናው ድርጅት ብዛቱን መግለፅ አስፈላጊ አይደለም ከውጭ የሄድነውም ጭምር እጃችንን በማውጣት ባዲስ መልክ ድርጅቱ ተዋቀረ። ደስ ያለውም የተከፋውም እንድ ላይ በመሆን በጉባኤው መዝጊያ አርበኛውን በቅንነት ለማገልገል ሁላችንም ቆመን ቃል በመግባት ጉባኤው በሰላምና በፍቅር ተጠናቀቀ። ከዚህ በሁላ እንግዲህ አነ አቶ ኤልያስ ክፍሌና መሰሎቹ ወደ የአገሮቻቸው በሰላም ሲመለሱ ምን አይነት የበቀል እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ አስቡ። እንደተጠበቀው በተመለስን በሁለተኛው ሳምንት በሕይወት ያሉት የኮሚቴው ሊቀመንበር ኮሎኔል ጌትነት ሊበን ሁላችንን በቴሌ ኮንፈረንስ ስብሰባ ጠሩን። እንደምትገምቱት ከአርበኛው ፊት አይጥ የዋጠች ድመት መስለውና ሆነው የተገኙት ጀግኖቻችን ዋሽንግተን ዲሲ ሲገቡ ምን እንደሚሆኑ መግለጽ አያሻም።
  መቼም በኮንፈረንሱ ወቅት አብረን ተቀመጥን እንጅ ስብሰባው ሰብሰባ አይልነበረም ባለመጣጣም ተለያየን። የማይረሳ ቂምና በቀል ተይዞልና አነ አቶ ደምስና አቶ ኤልያስ ቀደም ሲል ድርጅቱን ያቆሰሉት በርካታ ናቸውና የቆሰለን አውሬ መግደል ቀላል ነው በሚል ተባባሪ ሽፍታ መፈላለግና ማሰላሰል ነበረባቸው። ያለ ችግር ያለ ውጣ ውረድ የሚፈልጉትን አገኙ አዘጋጅተዋልም። እንደተለመደው ባያሰሩም ኮሎኔሉ ቴሌኮንፈረንስ አሁንም ጠሩ መደማመጥ ግን አልተቻለም። ኮሎኔሉ በጣም ትሁትና ትግስተኛ ስለሆኑ እንደምንም ብለው በተቀረጹት አጀንዳዎች ላይ ማብራራት ጀመሩ። በዚህ መካከል በወቅቱ ፀሓፊ ሆኖ የተመደበ አንድ ለችግሮቹ ሁሉ መነሻ የሆነ ጥላ የለሽ ቀርፀ ቀሊል ለውሸቱ ልክ የለሽ የሆነው ፀሐፊ ተብየው በስብሰባው እሳት ለቀቀበት። ስድብም በመጀመሩ ኮሎኔል ጌትነት ሁለቱን ለጊዜው እንዲያግዱዋቸው ፀሐፊው አጥብቆ ጠየቀ ካልሆነ ግን ትቸው እወጣለሁ ብሎ አስጠነቀቀ።በዚህ መካከል አቶ ዘውዳለም ከበደና አቶ ስለሽ ጥላሁ እገዳዉ እንዳይፈፀም ተማፀኑ። የመልረሳው አቶ ዘውዳለም ያሉት አባባል አቶ ኤልያስ ክፍሌ ከታገደና ከወጣ የማይጠቅመን ሰው ቢሆንም የመጉዳት አቅሙ ግን ከፍተኛ ነው ብለው አሳሰቡ ። አቶ ስለሽ ጥላሁንም መታገድ የለባቸውም በሚል አሳሰበ።እስካሁን በሚያውቀው ውነታ ላይ እንደነ አቶ ኤልያስና ደምስ የሃሰት ጥላቻ ያላስተላፈው አንደበቱን የቆጠበ ብዕሩን ያልመዘዘው አቶ ስለሸ ጥላሁን ብቻ ነው።በውነቱ እሱም ያሰፈርኩዋቸውን ነገሮች ሁሉ እንደሚመሰክር አልጠራጠርም።ከእነሱ ጋር በጅምላ የተባረረ ሰው መሆኑ ቢታወቅም ማለቴ ነው። ትላንትና የ40 አመት የነበርነው ዛሬየ46 አመት የ50 የነበርነው ዛሬየ56 አመት ሽማግሌዎች ሆነናልና ኑዛዜም በመሆኑ ውነቱን ተናግረን ማለፍ ስለሚጠበቅብን አቶ ስለሽ መባረር ያልነበረበት የድርጅቱ ባለውለታ ነው።
  በኔ እምነት ለጊዜው ዋሽቶ መወንጀል የሚያስደስታቸው ወገኖች የሕሊና እረፍት ግን ፈጽሞ አይኖራቸውም። ከዚህ ከድርጅት ሲባረሩ የሚያዝኑትና የሚጎዱትም በቅንነት ያገለገሉት ድርጅቱ እንዲያድግ ገንዘባቸውን የከሰከሱ ለድርጅቱ ሲሉ ከወገናቸው ጋር የተጣሉ ትዳራቸውንም የፈቱ ሰዎች ናቸው እንጅ ለገንዘብ ብለው ገብተው ገንዘብ ቦጭቀው የወጡት ሌቦች አይደሉም። በቴሌ ኮንፈረንሱ ወቅት አቶ ስለሽ በስህተት 4 ይመስለኛል ሳይጨርስ እንደውጣም አስታውሳለሁ። ጥላ የለሽ ቀርፀ ቀሊሉም በጭራሽ የፈለገውን ይሁን እንጂ አብሬ አልሰራም ያለውን ቃል አንደማያጥፍ ሲረጋግጥ አማራጭ አልነበረምና ያቀረበውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ስብሰባውን እረግጦ ከሚወጣና ሁላችንም ከምንበታተን በሚል ያቀረበውን የእገዳ ጥያቄ መሰረት በማድረግ ታገዱ። አፋፍ ላይ የነበሩት ወንድሞቻችንም በሩ ሙሉ በሙሉ ተከፈተላቸው። በሰላም መቀጠል የማይችሉ መሆኑ ቢታወቅም የጥላየለሹ ባህሪ ግን እንዳልኩት በር ከፋች ነበር። ሰውየው ለመዋሸትና ችግር ለመፍጠር ልዩ ስልጠና የወሰደ ነው የሚመስል። እነዚህ የታገዱት ወገኖች እገዳውን በመቃውም ለድርጅቱ ሊቀመንበር ኤርትራ ደውለው ታግደናልና በቶሎ ለኮሎኔሉ ደውለህ እገዳውን አስነሳልን ይሉታል።እሱም በደንብ ያውቃቸዋልና ጀመራቹሁ? እንደምታስታውሱት ምንም አይነት መብት የለኝም በጉባኤው ራሳችሁ ያስወሰናችሁት ውሳኔ ነው። በነፃነት እንድንሰራ ጣልቃ እትግቡ ባላችሁት መሰረት መሰረት የተወሰነ ስለሆነ አይመለከተንም ይላቸዋል። አነሱም ንፍጣም ብለው ስልኩን ይዘጉና ወደ ሚያምኑበት ለኮሎኔል ፍፁም ይድውሉና ሁኔታውን ይገልፁለታል። እሱም እኔ በድርጅታችህ ውስጥ ምን አገባኝ፣ እኔም በስብሰባችሁ ውስጥ ነበርኩኝ እንደማስታውሰው በኛ ኮሚቴ ውስጥ ጣልቃ አትግቡብን ብላችሁ ወናችኋል ሰለዚህ ይህን ጉዳይ እንኳን እኔ ማዛውም የሚረዳችሁ አይመስለኝም! ብሎ መልስ ይሰጣቸዋል እነሱም የማይጠበቅ መርዶ ሆነባችው።
  ይቀጥላል…

 2. To Kassaye Mersha. Thank you.

  And Thank you who ever you are for sharing this article on this comment page. I recommend(Kassaye) to post the rest of the story as soon as possible. We hope Habesha will post your next article on its main page. Knowing all the facts will move our fight for freedom one step further. Deflectors like Demise are running out of options and they are resorting to desperate measures stop the next by our people to freedom.

 3. To Kassaye Mersha. Thank you.

  And Thank you who ever you are for sharing this article on this comment page. I recommend(Kassaye) to post the rest of the story as soon as possible. We hope Habesha will post your next article on its main page. Knowing all the facts will move our fight for freedom one step further. Deflectors like Demise are running out of options and they are resorting to desperate measures stop the next move by our people to freedom.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

1 × 3 =