ZeHabesha Ethiopian News | Latest News for All | 24/7

Video: Confessions of a TPLF Spy | by Sadik Ahmed


Video: Confessions of a TPLF Spy | by Sadik Ahmed

3 Comments

 1. ጊዜው መሸ እንጂ ማሞ ውድነህ እንደተረጎመው “የሰላይ ተሰላይ” የሚል መጽሃፍ ማንበቤ ትውስ ይለኛል። ምን ያላነበብኩት አለ “እንደወጣች ቀረችም ” ትዝ ይለኛል ። የቀድሞው የወያኔ ነገር አቀባይ የዘረዘራቸው ነገሮች ሁሉ ትላንትም ዛሬም በሥፋት ወያኔ የሚጠቀምባቸው አጥፊ ዘዴዎች ናቸው። በቃለ ምልልሱ የእንጅኒየር ሃይሉ ሻውል በወያኔ እጅ መንገላታት (ነሳቸውን ይማር) ሳስብ አንድ የቀድሞ የወያኔ ሰላይ ያጫወተኝ ትዝ አለኝ። ዶ/ር አስራትን ወያኔ ለማሰር ሲፈልግ የውሸት ወረቀት በመጻፍና ተመሳሳይ መሃተም በማስፈር ለእስር እንደዳረጋቸውና እንዳሰቃያቸው የሞታቸውንም መቃረብ ሲረዳ ከስር እንደፈታቸው ሲቃ በተሞላ ስሜት አጫውቶኛል። ወያኔ አረመኔ ነው ስንል ከሜዳ ተነስተን አይደለም። ሺህ ሁሴንን ወያኔ እንዳስገደላቸው ህዝባችን ጠንቅቆ ያውቃል። በሴራ ማስገደሉ አንሶ ሌሎችን በሰብብ ማስቃየቱና ማሰሩ ምን ያህል አጥፊ ድርጅት እንደሆነ ያሳያል።
  ዛሬ ወያኔ የሚፈነጭባት ከቁራሽ ተራፊዋ ሃገራችን በስውርና በይፋ ሰዎች የሚታፈኑባት፤የሚገደሉባት አንድ ነጠላ ድርጅት በትግራይ ህዝብ ስም የሚነግድባት ምድር ናት። ከገዳም ሰው አውጥቶ የሚገል፤ የገዳም ሃብትና ንብረትን የሚቀማና የሚያቃጥል፤ ሰውን በዘርና በሃይማኖት ከፋፍሎ ለአንድ እሳት በመስጠት ሂድና ቤታቸውን አቃጥሉ የሚል ከጣሊያኑ ሞሶሎኒ የከፋ ድርጅት ወያኔ ነው።
  አንድ በአ.አበባ የተፈጸመ ነገር ልንገራችሁ። ልጅ አባቱ ነጋዴ ስለነበሩ ከበፊት ጀመሮ የመነገድ ብልሃቱ ከፍ ያለ ነበር። ሳይታሰብ አባቱ ይሞታሉ። ታዲያ ልጆቻቸው አስከሬን ምርመራ በማለት ምርመራ እንዲካሄድ ተደርጎ ውጤቱ የልብ ድካም ነው የገደላቸው ተብሎ የነገራቸዋል። ሰውም በመሰባሰብ ወደ ትውልድ መንደራቸው በመውሰድ ይቀበራሉ። በወሩ የሆነ ስልክ ይደወልና እባክሽ ላገኝሽ እፈልጋለሁ ይላል ሰወየው የሟችን የመጨረሻ ልጅ። እርሱዋም እናትዋን አስከትላ በቀጠሮው ስፍራ ትደርሳለች። ቅብዝብዙ ሰውም የተጻፈ ወረቀት (በታይፕ) በሰው በኩል ለልጁቷ እንዲደርሳት ያደርጋል። ስትከፍተው እንዲህ ይላል። መጮህ መደናገጥ የለም። በዝምታ ይነበብ። ቻው ይላል። ባጭሩ ደብዳቤው አባታቸው በወያኔ ሰላዮች አለቅጥ ሃብታምና አማራ በመሆኑ ተፈርዶበት እንደሞተ እንጂ የልብ ድካም አለመሆኑን ይጠቁማል። አባት ከሞተ ከ10 አመት በህዋላ አንድ ልጃቸው የወጣለት ታጅር ይሆናል። የወያኔ የስለላ ድርጅትም ልክ እንዳባቱ ሞት ይፈርድበታል። በሚበላው ምግብ ውስጥ መርዝ በመቀላቀል ይገደላል። የአባትና ልጅ ጥፋታችው ከአማራ ብሄረሰብ መወለዳቸውና የወያኔን የጥቅል የንግድ ስራ መገዳደራቸው ነበር። እልፍ አሳዛኝና ዝግናኝ ወሬ ማካፈል ይቻላል። ግን ወላዋዩና ሃገር ከፋፋዮ ደራሲ ተስፋየ ገ/አብ በተገለገለባት አንዲት አማርኛ ሃሳቤን እዘጋለሁ። ” ህዝቡ እንኳን ቆሞ መሄድ እንዲችል፤ ለነገ ተስፋ እንዲኖረው መናገር የማልችላቸው የሚሰቀጥጡ ነገሮች አሉ”። ቃለ መጠየቁ ጥንቃቄ የተሞላበትና መጠየቅ ያለባቸውን ነገሮች ያስተናገደ በመሆኑ ሳዲቅ አህመድን በርታ አይዞህ እላለሁ።

 2. Ethiopian writers do not need to write fiction to write about crimes nowadays. The Ethiopia people see crime all around them each day because of woyane. Just to mention a few out of the countless crimes the people are forced to live with by Woyane.

  1.The government claims 100% people voted for them which is totally false.

  2.Churches and other religious institutions get embezzled all the time by Woyane supporters with noone dare say anything to stop them.

  3.You can buy anything you want including gold mines or oil mines in Ethiopia from the officials woyane put in power, you don’t have to pay taxes on the profit you make or you don’t have to report the amount of gold you mined to the governmentas long as you regularly pay bribe to the government officials .

  4. People get killed by woyane for defending their identity , their human rights and so on then the same person that killed the victim goes to the victim’s family members pretending to be concerned good samaritan law officer and offers to help the family search for the missing person just to make sure the family find the body and no reports gets written about the suspicious death while still pretending to be a search party not the murderer covering up evidences or other questions that might get raised by witnesses if the body was found without the murderers presence with other family members. Once the body was found with the murderer’s presence if the family tried to press charge the murderer would say it wasnot suspicious it looked like an animal killed him and case will not be opened to investigate the death. .

  5. Last but not least fraud especially bid rigging is considered a common practice in Ethiopia with majority of Woyane’s not even aware it is illegal since they did it in open for so long, even though fraud especially bid rigging is costing Ethiopia’s economy estimated to amount to billions of dollars each year .

 3. From GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay)

  በሰላዩ ላይ የታዘብኩዋቸው ሁለት ነገሮች፤-

  1- ኢንጂኔር ሃይሉ ሻውልን “በአንቱታ” በመጥራት “እሱ” ይላቸዋል። ወለየው ሟቹ “ሼክ ኑሩ” ን ግን “እሳቸው” እያለ በአክብሮት ይጠራቸዋል። ሰላዩ ወያኔ ያሳደረበት የሃይሉ ሻውል ጥላቻ አሁንም በሕሊናው ተቀርፆ ይሆን “እሱ” እያለ የሚጠራቸው? በ “እሱ” እና በ “እሳቸው” መካከል ልዩነቱ ኣያውቅም እንዳይባል፤ ሁለቱም አጠራሮች በሟቾቹ በሁለቱም የተከበሩ ሰዎች ላይ “እሱ” እና እሳቸው የሚሉ ቃላቶችን ተጠቅሟል። ነገሩ ምን ይሆን?

  2- በሃይሉ ሻውል ላይ ዘግናኝ ድብደባ/ግረፍያ/ተፈጽሞባቸው ነበር ሲል አድምጬዋለሁ። ይህ እኔ ለ፤መጀመሪያ ጊዜ ነው ያደመጥኩት። ካሁን በፊትም እንዲህ ያለ ዘገባ እንደተደረገ ያነበብኩ አልመሰለኝም። ከነበረም አንባቢዎች ጠቁሙኝ።

  3- የወያኔ ሰላዮች ሲከዱ እባካችሁ ፡ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ወይንም የሕግ ባለሞያዎች (የሕግ ባለሞያዎች እንኳ ለነገሩ እንጂ “ቀጤማዎች” ተብላችሁ ብትጠሩም አያንሳቸሁም ፡”ከንቱዎች” ናችሁ ማለቴ ነው፡ —-! በማግኘት ምስጢራዊ ቃለ መጠይቅ በማድረግ የፈጸሙዋቸው ወንጀሎች እና የተገደሉ ሰዎች እንዲሁም በእነማን አንደተገደሉ፤ ወይንም የደብዳቢዎች ስም ዝርዝር፤ ለአለም አቀፍ ክስ ወይንም ለመጪው ስርዓት እና ሕግ ለማየት እንዲመች ሰላዮቹ ጠቃሚ ነጎረችን አንዲነግሯችሁ አድርጉ። የራድኦ ቃለ መጠይቅ ለሕግ አስፈላጊነት የሆኑ ምስጢርን የማሰባሰብ ጥልቀት ሊኖሮው አይችልም።

  4- ውጭ አገር የምትኖሩ የሕግ ባለሞያዎች ፤ ሳትማሩ ብትቀሩ በተሻለ ነበር። ማፈሪያዎች ናችሁ። ገዳዮች በገፍ ካፍንጫችን ስር እየነሩ፤ አንዳንዱም አሁንም ከወያኔ ጋር ሆነው ጅራፋቸው ሲያጮሁ እንሰማለን። ሰላዮች፤ እና የወያኔ መንግሥታዊ ሥልጣን የነበራቸው/ሚኒሰትሮች ሁሉ በተቃዋሚ ሚዲየዎች ሆነው ሲያሾፉ፤ ሲዘልፉን፤ ፖለቲካዉን ሲተነትኑ (እነ ታምራት ላይኔ፤ ጅኖዲን ሰዶ፤ ኤርሚያስ ለገሰ፤ካሳ ከበደ፤ዳዊት ወልደጊዮርጊስ …አረ ስነቱ…..አረ ስንቱ…….. እናደምጣቸዋለን። እስከዚህ ድረስ በጣም የተናቃችሁ የሕግ ባለሞያዎች ባትማሩ በተሻለ ነበር። እነሲህ ሰዎች ወያኔ አንዲህ አደረገ፤አንዲህ አደረገ እንጂ አራሳቸው ሲፈጽሙት የነበረ ወንጀል እና አስከፊ አፈጻጸም እንዲነግሩን አልተደረገም። ምክንያቱም ፤ተቃዋሚ ሚዲየዎች፤ የፖለቲካ መሪዎች፤አክቲቪስቶች ወዳጆቻቸው ሆነዋል እና የሚተቻቸው ዜጋ የለም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አስገራሚ ነው።

  5- አመሰግናለሁ

  6- ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ / Editor Ethiopian Semay

Leave a Reply

Your email address will not be published.