The Habesha: Latest Ethiopian News, Analysis and Articles

English French German Hebrew Swedish Spanish Italian Arabic Dutch

Sport: የቢቢሲ የ”African Footballer of the Year 2012″ እጩዎች ታወቁ

(ዘ-ሐበሻ) በየዓመቱ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋቾችን በአድማጮቹ ድምጽ የሚመርጠውና የሚሸልመው ቢቢሲ ዘንድሮም ለ13ኛ ጊዜ 5 እጩዎችን አቅርቧል። “African Footballer of the Year” በሚል ከፈረንጆቹ ሚሊኒየም ጀምሮ መሰጠት የተጀመረው ይኸው የቢቢሲው ሽልማት ዘንድሮ ለእጩነት ካቀረባቸው መካከል 2ቱ ከአይቬሪኮስት (ኮትዲቭዋር) ናቸው። ቸልሲን ተሰናብቶ ወደ ቻይና በመጓዝ ለሻንጋይ ሽንዋ በመጫወት ላይ የሚገኘው ዲድየር ድሮግባ እና የማንቸስተር ሲቲው ሞተር ያያ ቱሬ ከኮትዲቭዋር ሲመረጡ የሞሮኮው የኑስ ቢሊሃናዳ፣ ኒውካስትል እየተጫወተ የሚገኝው ሴኒጋላዊው ባ እንዲሁም የዛምቢያው ክርስቶፎር ካአቶንጎ ናቸው። ቢቢሲ ከነዚህ ውስጥ BBC African Footballer of the Year 2012ን ለመሸለም አድማጮች እስከ ዲሴምበር 13 ቀን 2012 በቴክስት መልዕክት እና በኦንላይን ድምጽ መስጠት እንደሚችሉ አስታውቋል።

እስካሁን BBC African Footballer of the Yearን ያሸነፉት ተጫዋቾች እነማን ናቸው? እነሆ ዝርዝሩ።

2011 – Andre ‘Dede’ Ayew (Marseille & Ghana)

2010 – Asamoah Gyan (Sunderland & Ghana)

2009 – Didier Drogba (Chelsea & Ivory Coast)

2008 – Mohamed Aboutrika (Al Ahly & Egypt)

2007 – Emmanuel Adebayor (Arsenal & Togo)

2006 – Michael Essien (Chelsea & Ghana)

2005 – Mohamed Barakat (Al Ahly & Egypt)

2004 – Jay Jay Okocha (Bolton & Nigeria)

2003 – Jay Jay Okocha (Bolton & Nigeria)

2002 – El Hadji Diouf (Liverpool & Senegal)

2001 – Sammy Kuffour (Bayern Munich & Ghana)

2000 – Patrick Mboma (Parma & Cameroon)

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top