ZeHabesha Ethiopian News | Latest News for All | 24/7

Hiber Radio Special Interview with Eskinder Nega


Hiber Radio Special Interview with Eskinder Nega

Read Aloud:   Manchester United Vs Arsenal - Video Highlights

5 Comments

 1. ይሄ መቶ ቀን የሚባል ነገር ከየት መጣ?

  የፈረደባቸው አሜሪካኖች አንድ ፕሬዚዳንት መርጠው ስራ ካስጀመሩት በሗላ በምርጫው ወቅት እፈጽማቸዋለሁ ብሎ ቃል ከገባቸው ጉዳዩች ውስጥ ምን ያህል ፈጸመ – ለወደፊቱ አያያዙስ ምን ያሳያል የሚል ጥያቄ አንስተው ይወያያሉ:: ይህ መቶ ቀን የሚባል ነገር በእኛ ሁኔታ ከየት እንደመጣ ባላውቅም አሜሪካኖች ብልሆች ስለሆኑ መቶ ቀን ያሉበት መክንያት እንዳላቸው አውቃለሁ::

  ታሪኩ እንዲህ ነው:: በፕረዚዳንት ፍራንክሊን ሩዝቤልት በተጠራ ልዩ ስብሰባ ኮንግሬስ ከሚያዝያ 9, 1933 እስከ ሰኔ 16, 1933 በጣም አስፈላጊ የነበሩ ማህበራዊ ህግጋት ያወጣል;; ቀናቱ ሲደመሩ መቶ በመሆናቸውና በጣም አስፈላጊ የነሆኑ ማህበራዊ ህግጋት በመውጣታቸው ዋቅቱ መቶ ቀናት በመባል ተጠራ:: ከዚያ በሗላ በተለምዶ አንድ ፕሬዚዳንት ከተመረጠ በሗላ ባሉት መቶ ቀናት የፈጸማቸውን ነገሮች በምርጫ ወቅት ከሰጠው የተስፋ ቃል ጋር መመርመር ተጀመር:: የመቶ ቀን ታሪክ ከፈረንሳይ ታሪክ ጋርም የተያያዘ ቢሆንም በአሜሪካ የራሱ ታሪክ ይዞ ብቅ ብሏል::

  እኛ መቼም አሜሪካ የተባለ ነገር ላይ ሁሉ መንጠልጠል ስለምንወድ “መቶ ቀን” የሚለውን ሃሳባቸውን ዝም ብለን በጠራራ ጸሃይ የቀማናቸው ይመስለኛል:: አሁን የዳያስፖራውን መድረክ በማናለብንነት የተቆጣጠሩ የሚመስሉት “አምስቱ” የግንቦት 7 / ኢሳቴ የፖለቲካ ዜና ተንታኞች ይህንኑ የመቶ ቀን ነገር እየተወለካከፉ ሲወጡበት ሲወርዱንበት ነበር:: ምንያድርጉ? ሃይ የሚላቸው ሰው የለ::

  አሁንም እስከንድር በግንቦች 7 / ኢሳቴ ተንታኞች መንገድ የነጎደ ይመስላል:: ልጁ እንዃ ከግንቦች 7 / ኢሳቴ ተንታኞች የተሻለ ትምህርትም- እውቀትም ልምድም ነበረው:: በዚህ ጉዳይ ምን እንደነካው አላውቅም::

  ለማንኛውም ዶ/ር ዓብይ አሀመድ እንደአሜርካ ፕሬዚዳንታዊ ተመርጮች የተመረጠ ሰው አይደለም:: ሁለት መቶ በማይሞሉ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚዎች የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስራ የተሰጠው ሰው ነው:: እነዚህ ሁለት መቶ በማይሞሉ ሰዎችም ቢሆኑ አስር ሚሊዩን ይደርሳሉ በሚባሉት የኢህአዴግ አባላት ተወካዩች ነጻ ውድድር ተደርጎ የተመረጡ አይደሉም:: ይህም ሆኖ ዶ/ር ዓብይ በምርጫ ወቅት እፈጽማቸዋለሁ ብሎ ቃል የገባባቸው ጉዳዩች የሉም:: እውነታው ይህ ከሆነ ከመቶ ቀናት በሗላ በምንድነው የሚላካው?

  እንደሚገባን ከሆነ ዶ/ር ዓብይ ይለካል የሚባለው ሃገር ውስጥና ዳያስፖራ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ይፈጸሙልን ብለው የጠየቋቸው ነገሮች መፈጸም አለመፈጸም ይመስላል:: ሰውየው ደግሞ ነገሮችኡ እስከመኖራቸውም የሰማ አይመስልም:: ስለሆነም በድርጅቱ ፕሮግራም ገፍቶበታል::

  ነገሩ እንዲህ ከሆነ የመቶ ቀነ ነገር በተለመደው የፖለቲካ ጥራዝ ነጠቅነት የተሰነዘርና እንዲያው ምንም ማሰብ ሳይታከለበት የሚደገም – የሚደጋገም ነው;;

  እስክንድር ማሰብ ስለምትችል እነዚህ ሃገር ውስጥና ዳያስፖራ የሚገኙ ተቃዋሚዎች የሚሉትን ዝም ብለህ አትድገም::

  ቢያንስ አንዳንድ የተከበረ ቦታ ስትገኝ መለዩህን ማውለቅ እንደወትሮው በነጻነት ለማሰብ ይረዳህ ይሆን?

  በቸር ቆየን::

 2. Dennbitoo Dinno,

  Overall, good observation.

  Just to add a point on Eskinder’s cap. From
  the logo, his cap is Nike which is an American athletic shoe and clothing manufacturer enterprise. The logo is one of the most recognizable and profitable brand worth $26 billion alone.

  I doubt if Eskinder is paid for carrying and flashing Nike’s logo around. Nike would, in fact, be surprised if a democracy and human rights activist carries their logo wherever he goes. Why? Because Nike has serous human rights issues itself.

  Some years ago, reports suggested that Nike has “contracted with more than 700 shops around the world and has offices located in 45 countries outside the United States.” When asked about the companies it works, it was hesitant to disclose information. It finally released the information in which it admitted that two-thirds of its factories do not meet the company’s standards for worker treatment. They were found to have have violated minimum wage and overtime laws, poor working conditions and exploitation of cheap overseas labor. Nike was also criticised for the use of child labour.

  So, why does Eskinder who is an advocate carry Nike’s logo whereever he goes particularly in international conférences where people opposed to Nike’s activities particiapate? Maybe he thinks it is no big deal and he puts it on simply because it fits well. But other people are watching and it is important for them.

  Tell Eskinder to get another cap.

  Cheers!

 3. ድንቢጡ፣
  ዶ/ር አብይ እንደ አሜሪካ በሕዝብ ድምጽ ስላልተመረጠ በመቶ ቀን በሁለት መቶ ቀን ማለት ትርጕም የለውም ማለትህ ትክክል ነው። ጉዳዩ የቀኑና የወሩ ገደብ ሳይሆን በሕዝብ ድምጽ አለመመረጡ ነው፤
  ኮፊያ አለማውለቁን እንደ ትልቅ ነገር አልቆጥረውም፤ ይልቅ ኩኩሽ እንዳስረዳችው፣ ናይኪ የባርያ ስርዓት በመሰለ አኳኋን በኤስያ ምርቱን እያካሄደ ነው። እስክንድር ይህንን አስተውሎ ለግፍ ሬክላም እንዳይሆን መጠንቀቅ አለበት። እንዲያውም ትግሉን በሚያራምድና በሚያስተዋውቅ ምልክት መተካት ይጠቅማል። ምልክቱንም ዜጎች አስተዋጾ እንዲያደርጉ ቢደረግ ይበልጥ ጥሩ ይሆናል።

  በተረፈ “እስከንድር በግንቦች 7 / ኢሳቴ ተንታኞች መንገድ የነጎደ ይመስላል:: ልጁ እንዃ ከግንቦች 7 / ኢሳቴ ተንታኞች የተሻለ ትምህርትም- እውቀትም ልምድም ነበረው:: በዚህ ጉዳይ ምን እንደነካው አላውቅም::” ማለትህ ለማያያዝ እንዳይሆን ሰጋሁ። እስክንድር እንደ ግንቦት 7 በመሣሪያ ትግል አያምንም፤ ደጋግሞ ገልጾታል።

  “የዳያስፖራውን መድረክ በማናለብንነት የተቆጣጠሩ የሚመስሉት “አምስቱ” የግንቦት 7 / ኢሳቴ የፖለቲካ ዜና ተንታኞች ይህንኑ የመቶ ቀን ነገር እየተወለካከፉ ሲወጡበት ሲወርዱንበት ነበር:: ምንያድርጉ? ሃይ የሚላቸው ሰው የለ::” ያልከው ትክክለኛ ትዝብት ነው። ደግነቱ፣ መድረኩን የተቆጣጠሩት የሚመስላቸው እነርሱን እንጂ ብዙሓኑን አይደለም።

 4. አለም – አፌ ቁርጥ ይበልልሽ !

  እውነትም እንዳልሽው እስክንድር የናይክ ምልክት ያለበትን ኮፍያውን ወደዚያ መወርወር አለበት:: አድማጭና ትሁት ቢሆን እስካሁን በማወቅም ሆነ ባላማወቅ ለናይክ ለሰራው ማስታወቂያ በናይክ እኩይ ድርጊት ቅሬታ ያላቸውን ሁሉ ይቅርታ ቢጠይቅ ደስ ይለኛል:: በናይክ ድርጊት ቅሬታ ካላቸው ውስጥ አንዷ በመሆኔ ላለፈው ጥፋቱ ካሳችን አንቺ እንዳልሺው ዲሞክራሲናን ሰብዓዊ መብትን የሚመያላከት ኮፍያ ወይም ሌላ ነገር ሲያደርግ ነው:: ይህን ካልወደደ ዝም ብሎ ምንም ምልክት የሌለበት ኮፊያ ቢያደርግ የሚመረጥ ይመስለኛል:: እንደኔ እንደኔ እስከጭራሹ ኮፍያ ባያደርግ ወይም ለኮፊያ ቦታና ጊዜ ቢመርጥ ደስ ይለኛል:: ሁኔታው በራስ መተማመንን ያመላክታልና:: እሱ ደግሞ በራስ የመተማመን ችግር የለበትም:: የማያውቁት በተለይ የውጭ ዜጎች በዚህ ሊሳሳቱ ይችላሉ:: እኛ ደግሞ አንድ ተሟጋቻችንን በተልካሻ ምክንያት ልናጣው አንፈልግም::

  እህቴ ሆይ!

  “እስክንድር እንደ ግንቦት 7 በመሣሪያ ትግል አያምንም፤ ደጋግሞ ገልጾታል ” ባልሽው እርግጠኛ አይደለሁም:: ሃገር ወስጥ በሚካሄደው ሽግግር መሳሪያ ያነሱትም መሳተፍ አላባቸው ሲል የሰማሁት መሰለኝ :: ይህን ለማለት መጀመሪያ እነዚህ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ ብቻ ለመታገል መቁረጣቸንና መሳሪያቸውን ማስቀመጣቸውን በማያሻማ ቋንቋ ለመላው ኣለም እቅ አላባቸው:: ስለተኮስንበት ፈርቶ አስገባን በሚል መንፈስ ወደሃገራችን እንዲገቡና ከገቡም በኋላ እያስፈራሩ ስልጣን እንዲካፈሉ አንፈልግም:: ይህ ስልጣን በመሳሪያ ሃይል ከመቀማት አይለየም:: እናም እስክንድር ሰላማዊ ትግል ብቻ እንደሚደግፍ ግልጽ የሚሆነ የትጥቅ ትግልን ሲያወግዝና ከዚያ መንገድ አንዋጣም በማለት በባዶ ሜዳ ያዙን ልቀቁን የሚሉት ወደሳላማዊ ትግል እንዲመለሱ ጥሪ ሲያደርግ ብቻ ነው:: ሰላማዊ ትግል አሸንፎ የትጥቅ ትግል የሚባለውን ገና ብድግ ሳይል በባዶ ስላስቀረው እስክንድር ቢያወግዝው የሚደርስበት ነገር ያለ አይመስለኝም:: የትጥቅ ትግል እንደፉከራው ተስፋፍቶ ቢሆን ኖሮ አሁን የደረስንበት ደረጃ ባልደረስን ነበር:: እንዲያውም ትግሉን በመከፋፈል – የሰላማዊ ትግሉን ጎራ በማዳከምና ቁሳቁስ በመቀማት ብዙ በደል ያደረሰ ሃይል በመሆኑ ወደፊት መጠየቁ እይቀርም::

  ( “አምስቱ” የግንቦት 7 / ኢሳቴ የፖለቲካ ዜና ተንታኞች) መድረኩን የተቆጣጠሩት የሚመስላቸው እነርሱን እንጂ ብዙሓኑን አይደለም” ላልሺውም ቢሆን እርግጠኛ አይደለሁም:: ለማንኛውም በዚህ ጉዳይ ሰሞኑን እመለስበታለሁ:: እስከዚያው ቻው!

Leave a Reply

Your email address will not be published.