ZeHabesha Ethiopian News | Latest News for All | 24/7

Hiber Radio: በርካታ አርቲስቶች የዘመን መለወጫ በዓል ኮንስርቶችን በመሰረዝ ከህዝቡ ጎን መቆማቸው በሃይማኖት አባቶች ዘንድታላቅ አድናቆት ተቸራቸው፣ አቶ ዘመነ ምህረት ሕጋዊው የመኢአድ ም/ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የአገዛዙ ደህነቶች የፓርቲውን አመራሮችና አባላት እያሳደዱ ነው፣በብር ሸለቆ ከአማራ ክልል የታፈሱ ወጣቶች የማሰቃየት እርምጃ እየተፈጸመባቸውና የማያውቁትን መርፌ በግዳጅ መወጋታቸው ተገለጸ የሚሉና ሌሎችም

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas/hiber-radio-091116
የህብር ሬዲዮ መስከረም 1 ቀን 2009 ፕሮግራም

ጥቁር ዕንቁጣጣሽ አዲሱን ዓመት የለውጥ ዘመን ያድርግልን!

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

< … ትላንት ንጹህ የሆኑትን ያለወንጀላቸው አስረው ካሰቃዩዋቸው መካከል ጥቂቶቹን የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትን ጭምር ፈተው ፕሮፖጋንዳ ለመስራት ሲራወጡ ዛሬ ደግሞ ይሄው እኛን ሕጋዊውን የመኢአድ አመራሮች በደህነት እያሳደዱ ነው…የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይዘናጋ የጀመረውን የለውጥ ትግል በአንድ ላይ አጠናክሮ ይሄን የግፍ ስርዓት ማስወገድ አለበት።እነሱ እኛ ስልጣን ከለቀቅን አገሪቱ ትጠፋለች የሚሉት ምነው ኢትዮጵአን እኮ እነሱ አይደለም ጠፍጥፈው የሰሯት ሕዝቡ እነዚህን… > አቶ ለገሰ ወ/ሃና የሕጋዊው መኢአድ ም/የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ከህብር ሬዲዮ በአዲሱ ዓመት የሚደርስባቸውን ማሳደድ አስመልክቶ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

< …እነ ርዮት እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ሲፈቱም በሌላ በኩል ሌሎችን ለማሰር ሲሩዋሩዋጡና ሲያስሩም ነበር።እነዚህ አስቀድሞ መታሰር የማይገባቸው ሰላማዊ ጥያቄ ያቀረቡ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ውስጥ የተፈቱትም ሆነ ሌሎች አብረው በተፈቱት ፕሮፖጋንዳ መስራት ማንንም በዚህ አያታልሉም አውሮፓዎቹም አውቀው እንጂ ስሌአንዳንዱ የግፍ እርምጃ በቂ እውቀት አላቸው…በዚህ ወር መጨረሻ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ስብሰባ አለ በዚያ ላይ ንጹሃንን በግፍ የሚገለው ስርኣት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የተጀመረ ጥረት መጠናከር አለበት ኢትዮጵያውያንም በጋራ በብዙ ሺህ ፊርማቸውን አሰባስበው ጥያቄ ማቅረብ አለባቸው…>

አቶ ያሬድ ሀ/ማርያም በቤልጂየም የሚገኘው ስብስብ ለሰብኣዊ መብት ለኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ዳይሬክተር አስራ አምስት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ለተመድ ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ በወቅታዊ ጉዳይ ተወያይተን ከሰጡን ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋ ፤የውጪው አለም እና ሰሞነኛው የመብት ተሞጋቾች ምላሾች ሲዳሰሱ (ልዩ ጥንቅር)

የኢትዮጵያ ቀን በቬጋስ ለ10ኛ ጊዜ ሲከበር በአገር ቤት በግፍ የተገደሉት ታስበዋል ስለ በዓሉ የኮሚኒቲው አመራሮች የሰጡት ማብራሪያ(ልዩ ቃለ መጠይቅ ከኮሚኒቲው የቦርድ አባላት መካከል ከሁለቱ ጋር)

ዜናዎቻችን

በርካታ አርቲስቶች የዘመን መለወጫ በዓል ኮንስርቶችን በመሰረዝ ከህዝቡ ጎን መቆማቸው በሃይማኖት አባቶች ዘንድታላቅ አድናቆት ተቸራቸው

የሃይማኖት አባቶች ሃዋሪያዊ ተልእኮቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበላቸው

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አዲሱን ዓመት ጥቁር ለብሰው በአገር ቤት ያለውን ግድአ በመቃወም ተሰባስበው በተለያዩ ከተሞች አሳለፉ

አቶ አመነ ምህረት ሕጋዊው የመኢአድ ም/ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ደህነቶች የፓርቲውን አመራሮችና አባላት እያሳደዱ ነው

የፓርቲው የአዲስ አበባ ም/ቤት አባልና የሕዝብ ግንኑነት ሀላፊ ታሰረ

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መንግስት ለሕዝቡ የመብት ጥያቄ የአፈ ሙዝ ምላሽ ሊሰጥ አይገባም ሲሉ ጠንካራ መግለጫ አወጡ

በአማራ ክልል ወጣቶች በዘመቻ ማፈሱ ቀጥሏል

በብር ሸለቆ ከአማራ ክልል የታፈሱ ወጣጦች የማሰቃየት እርምጃ እየተፈጸመባቸውና የማያውቁትን መርፌ በግዳጅ መወጋታቸው ተገለጸ ድርጊቱን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያጣራ ተጠይቋል

ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ከብራዚል ወደ አሜሪካ ተሻገረ ሰሞኑንም ዋሽንግተን ላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና ያቀርባል

ኢትዮጵያዊው የማርሻል አርት ሻምፒዮና ደ/ኮሪያ ላይ የሕወሃት /ኢሃዲግ ስንደቃላማን ማየት አልፈልግም አለ

አሜሪካዊው እጩ ፕ/ት ዶናል ትራምፕ ስልጣን በያዝኩ ማግስት በርካታ ጄኔራሎችን እጠራርጋለሁ ማለታቸው ታላቅ መደናገጥ ፈጠረ

የቀድሞው ሪፓብሊካን የውጭ ጉ/ሚ/ር ኮሊን ፓወል እንደ ሂላሪይ ክሊንተን ሁሉ የመንግስት መረጃዎችን በግል ኢሜላቸው ይጠቀሙ እንደነበር አመኑ

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሴት ልጅ በእንግሊዝ መንግስት ላይ የመስረተችው ክስን ፍ/ቤት ውድቅ ማድረጉ በቤተስቡ ላይ ታላቅ ሃዘን ፈጠረ

“ፍ/ቤቱ የስብአዊነት ጉዳይን ከግንዛቤ ውስጥ የከተተ አልመሰለኝም“የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወ/ሮ የምስራች ሃ/ማርያም

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.