የዘሐበሻ የዕለቱ ዜና እና የኢትዮጵዊያን አመለካከት

የኦዲፒ ከኦሮሞ ፓርቲዎች ጋር አብሮ የመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

6 mins read

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።
Image may contain: 17 people, people standing
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢህአዴግና የኦዲፒ ሊቀ መንበር እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኦዲፒ ምክትል ሊቀ መንበርና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ሌንጮ ለታን ጨምሮ በርካታ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፥ አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ባህል እና ሀሳብ እንደሌለው መገዳደል እና መሰዳደብ ትክክል አይደለም፤ ፖለቲካችንን ማዘመን ይጠበቅብናል ብለዋል።
Image may contain: 2 people, people sitting
ባሉን ሀሳቦች ላይ በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየት ህጋዊ በሆነ መንገድ ፍላጎታችንን ከግብ ማድረስ እንችላለን ሲሉም ተናግረዋል።
የፖለቲካ ሀሳቦቻችንን ለህዝብ ለመግለፅ እና ለመታገል የሰው ልጅ መታሰር፣ መንገላታት እና መጎዳት የለበትም፤ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተወያየን መስራት እንችላለን የሚለው ትልቅ ሀሳብ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
ይህ ሀሳብ እዚህ ብቻ የሚቀር ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ ለሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶችም የሚሰራ ይመስለኛል ብለዋል በንግግራቸው።
Image may contain: 2 people, people sitting
“በውስጡ ሰላም የሌለው ሰው ለሌላው ሰላም መስጠት አይችልም፤ ለራሳችን የተሻለ ሀሳብ ከሌለን ለሌሎች ማካፈል እንችልም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ስለዚህ እየተወያየን እና እርስ በእርስ እየተማማርን የሀገራችንን ፖለቲካ ለማዘመን መወያየትና በጋራ መስራት በጣም ወሳኝ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ከ30 እና 40 ዓመታት በፊት ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎች አሁን

ኤፍ.ቢ.ሲ