የዘሐበሻ የዕለቱ ዜና እና የኢትዮጵዊያን አመለካከት

የሟቾች ቁጥር 48 ደረሰ

5 mins read
1

BBN መጋቢት 3/2009 | ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘዉ ቆሼ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ላይ በተነሳው የቆሻሻ ክምር መደርመስና የመሬት መንሸራተት የ15 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የአዲስ አበባ ከንቲባ ዲሪባ ኩማ አስታወቁ። ላለፉት50 አመታት በቆሻሻ መጣያነቱ የሚታወቀዉ ይህ ቦታ እስከ 300,000 ቶን የሚደርስ ቆሻሻ በየአመቱ እንደሚጣልበት ይታወቃል። የቆሻሻዉ ክምር በተገቢው መልኩ ባለመያዙ የመሬት መንሸራተቱ መከሰቱን የ አካባቢዉ ነዋሪዎች ለመገናኛ ብዙሗን ማስረዳታቸዉ ተገልጿል።

37 ሰዎች ከቆሻሻዉ አደጋ መዳናቸዉን አሶሸት ፕሬስ ካወጣው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል። በርካቶች በዚህ የቆሻሻ ክምር ዉስጥ ተሰዉረዉ አደጋ ደርሶባቸዋል የሚል ስጋት አለ።
ከአራት ሚሊዮን የሚበልጡ የአዲስ አባባ ነዋሪዎች ቆሻሻ የሚጣልበት ቦታ ላይ ቁጥራቸዉ እስከ 500 የሚደርሱ ሰዎች ቆሻሻዉን በመለየት፣ በመመነጣጠልና በመልቀም እንደሚተዳደሩ ታዉቋል። በዚህም የቆሻሻና የመሬት መንሸራተት አደጋ በብዛት ሰለባ የሆኑት በአካባቢው በደሳሳ ጎጆ ዉስጥ የሚኖሩ ደሃና ለፍቶ አዳሪ ሰዎች መሆናቸዉ ታዉቋል።

የቆሼ የቆሻሻ መጣያና ማከማቻ ቦታ ሊያመጣ የሚችለዉ አደጋ ቀደም ተብሎ የተገመተ ቢሆንም፤ የሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላቶች ተገቢውን ስራ ባለመስራታቸዉ አደጋዉ ሊከሰት መቻሉን በሐዘን የሚያሰረዱ ብዙ ናቸዉ። የመሬትና የቆሻሻ መንሸራተቱ ሲከሰት በስፍራዉ 150 ሰዎች እንደነበሩ የታወቀ ሲሆን ከነዚህ 48ቱ መሞታቸዉ፣37ቱ መዳናቸዉ ሲታወቅ ስለተቀሩት ሰዎች ሁናቴ ይፋ የሆነ መረጃ ከ እዲስ እበባ ማዘጋጃ ቤት አልተለቀቀም::