ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ከውጭ ኃይሎች ጋር ጦርነት ብታደርግም፤ ጦርነት ትርፍ እንደሌለው ትረዳለች ብለዋል።
ኢትዮጵያና ሱዳን ወደ ግጭት እንዲገቡ በማድረግ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሰሩ ሶስተኛ ወገኖች እንዳሉ ገልፀው፤ ኢትዮጵያ የጦርነት አማራጭ እንደማትከተል አክለዋል።
የኢትዮጵያና ሱዳን ሕዝቦች ረጅም ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው በመሆናቸው የጋራ ዕድገት እንጂ ጦርነት እንደማይፈልጉም ነው የገለጹት።
በአንፃሩ ሱዳን በድንበር አካባቢ አሁንም በተጠናከረ ሁኔታ ጦሯን እያንቀሳቀሰች መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለሠላምና ዲፕሎማሲ ቅድሚያ ትሰጣለች ያሉት ቃል አቀባዩ፤ የሱዳን ጦር ወደ ድንበሯ ጥሶ በመግባት እያደረገ ያለውን ሕገወጥ እንቅሰቃሴ መታገሷ ከፍርሃትና ከመወላወል ጋር የተገናኘ እንዳልሆነ ገልፀዋል።
እ.አ.አ በ1902 የተደረገውን ድንበር የማካለል ታሪክ ተከትሎ በተለያዩ ጊዜያት የተጀመሩ የጋራ የድንበር ማካለል ሠላማዊ እንቅስቃሴዎችን በመመለስ የሁለቱን አገራት የድንበር ችግር መፍታት ተገቢ እንደሆነም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢዜአ