የዘሐበሻ የዕለቱ ዜና እና የኢትዮጵዊያን አመለካከት

የትክከለኛ ኢትዮጵያውያን መንፈስና የንጹሐን ደም ፍትሕ! – ሰርፀ ደስታ

23 mins read
4

ዛሬ ባየሁት ነገር እጅግ የተደበላለቀ ሥሜት ነው የተሰማኝ፡፡ የአዛውንቱ ስብሀት ሲሰሩ ከኖሩት አስከፊ ድርጊት አንጻር መያዛቸውና ለፍርድ መቅረባቸው ጥሩ ሆኖ ሳለ በዚህ እድሜ ያለ ሰው በእንዲህ ያለ ሁኔታ መገኘቱ እጅግ አሳዝኖኛል፡፡ ለአእምሮም ሰላም አይሰጥም፡፡

በሌላ መልኩ የተያዙበት ሁኔታ እጅግ አርክቶኛል፡፡ ይሄን አይነት ፍትሕ ያለው ሕሊና አሁንም በትክክለኛ ኢትዮጵያኖች ዘንድ መኖሩ ያስደስታል፡፡ እነ ስብሐት ከፈጸሙት አስከፊ ድርጊታቸው አንጻር በሌሎች አገሮች ያየንውን አይነት ነገር አልገጠማቸውም፡፡ በሌሎች አከሮች ቢሆን እንኳን ከዛ ዝንጀሮ ከማይሞክረው ቋጥኝ ተንከባክቦ ማውረድ ይቅርና ሜዳ ላይ በሠላም ቢያገኛቸው እንኳን ሊፈጠር የሚችለውን ለማስተዋል በኢራቅ በሳዳምና በሊቢያ በጋዳፊ የሆነው ማየት በቂ ነው፡፡ በኢራቅ ሳዳም በአሜሪካኖች በመያዙ እስከፍርድ ቢደርስም የያዙት ኢራቃውያን ቢሆኑ ኖሮ ምን ሊያደርጉት እንደሚችሉ እንገምታለን፡፡ በኢትዮጵያም ዛሬ አዛውንቶቹን የያዟቸው የትክክለኛ ኢትዮጵያዊ ስነልቦና በመኖሩ እንጂ ስብሐት ይመሩት የነበረው የወያኔ ቡድን ሆኖ ቢሆን ባለድሉ ብዙ የከፋ ለአእምሮ የቀፈፈ ድርጊትን እናይ ነበር፡፡ በእርግጥም በማይካድራ ምንም በማያውቁ ሚስኪኖችና በመከላከያው ሰራዊቱ ላይ የፈጸሙት ብቻ በቂ ነው፡፡ የ30 ዓመቱን አረመኔነት ግፍ ትተን፡፡ ይሄ አረመኔነትን ግን በራሳቸው ብቻ አላስቀሩትም እጅግ ከፍተኛ ወደሚባል ሕዝባችንም አጋብተውት ይሄው ዛሬ የምናየውን ዘግኛኝ አረመኔነት እያየን ነው፡፡

ትክክለኛው  ኢትዮጵያዊ ሕሊና ያለው ዛሬ  አዛውንቱን የያዟቸው እንደበቀለኛ የከፋ ነገር ሲያደርጉባቸው ማየት ይቅርና ትንሽ እንኳን ሲያንገላቷቸው ቢያይ በሠራዊቱ ላይ እጅግ በተቆጣ ነበር፡፡ ይህ በሐይማኖት፣ በባህልና በልዕልና ጀግና የሆነ የኩሩ ሕዝብ ባህሪ ነው፡፡  ተሸንፎ እጅህ የወደቀን ጠላት ማሰቃየት በእርግጥም የወራዶቻና የፈሪዎች ባሕሪ እንጂ የጀግኖች ባሕሪ አደለም፡፡ ይህ መንፈስ በኢትዮጵያ በሕዝብ ደረጃ ያለ እንጂ የአንዳንዶች ብቻ አልነበረም፡፡  ወያኔ ብዙውን ትውልድ ከመበከሏ በፊት፡፡ የወያኔም በሉት የኦነጋውያን ወይም ሌሎች አረመኔነት ዋነኛ ምንጩ የፈሪና በበታችነት ስሜት የሚማቀቅ አእምሮ ነው፡፡ አሁንም ትግላችን መሆን ያለበት ትውልድ በእነዚህ አረመኔዎች አስተሳሰብ ይበልጥ እንዳይበከል የተበከለውንም ማከምና ማዳን ነው፡፡ በስልጣን ያሉት ከአሳዳጊያቸው የወረሱት ስለሆነ እነሱ ላይ ጊዜ ማጥፋት የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ብዙ እድል አግኝተዋል ግን ሊጠቀሙበት የፈለጉ አልመሰለኝም፡፡ ይሄ ዛሬ እነሱ ዋና የሆኑበት ድል ከወያኔ ጋር አብረው የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያሰቃዩ እንደነበሩ ሊታወቅና ይሄ የእነሱ ሳይሆን የጀግና መንፈስ ያለው ኢትዮጵያውያንን በደል ከላይ ሆኖ የሚመለከተው አምላካቸው በአይናቸው ፊት ጠላቶቻቸውን ያዋረደላቸው መሆኑ ይሰመርበት፡፡ እንጂም ከወያኔ ጋር ዋና ገዳይና አስገዳይ ሆናችሁ የነበራችሁትን ጊዜያችሁ እየተቆጠረ እንጂ ቀጥሎ በእናንተም መምጣቱ አይቀሬ ይመስላል፡፡  ከወያኔ የወረሳችሁትን እንደወረደ ዛሬም በሕዝብ ላይ እያሴራችሁና በወያኔ ሕግና ስርዓት ስልጣን ላይ ተቀምጣችሁ የወያኔ ያህል እንኳን ጊዜ ያላችሁ አይመስለኝም፡፡ ችግሩ እግዚአብሔር ሲቆጣ እንዲህ ነው፡፡ እንዳታስተውል ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ይሰጥሀል በራስህ ጊዜ በሰራሀት ሴራ ትወድቃለህ፡፡ ይገርማል፡፡

እስኪ አንድ ነገር ልጠይቅና መልሱልኝ፡፡ መቼም የወያኔ ባለስልጣን ወንጀል ያልሰራ አልነበረም፡፡ ሊያውም ዘግናኝ ወንጀል፡፡ እንደው በሰውኛው ሊያውም ዛሬ እነሱ ያሳደጓቸው ስልጣን ላይ ሆነው ምን አልባት እንደነ ጌታቸው አሰፋ የተባሉት ለፍርድ ቢቀርቡ እንጂ ቀሪዎቹ በንጹሐን ላይ ስላደረጉት የ27 ዓመት አረመኔያዊ ግፋቸውና አገሪቷን ዘርፈው ስለአካበቱት ሀብታቸው ይጠየቁ ነበር? አይመስለኝም፡፡ በተለይ አዛውንቱ ስብሐት ስለሰሩት በደል ሳይዳኙ እንደልባቸው ኖረው መጨረሻ እዛው እውነተኛው ዳኛ ጋር ይቀርቡ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ግን የፈለገው በምድር ግፍ የፈጸሙባቸውም ፍትሀቸውን እንዲያዩ ሌላውም በኢትዮጵያ ምድር የእግዚአብሔር እጅ እንደተዘረጋች እንዲያውቅና እንዲጠነቀቅ ይሄ ሁሉ ሆነ፡፡ አንዳቸውም ለሰሩት ሥራ በምድር ዋጋ ሳይከፍሉ እንዲያልፉ አልፈቀደም፡፡ ብዙዎች አንተ እያለህ ይሄ ሁሉ ግፍ እንዴት ይፈጸማል እያሉ አንብተውበታልና፡፡ እግዚአብሔር እንደሰው አይደለም፡፡ መስፈሪያው ልዩ ነው፡፡

በአንጻሩ እነ በረከት ስምዖንና ክንፈ ዳኛው ምንኛ እድለኞች እንሆኑ አስተዋልን፡፡ ቀድመው ወደ እስር ባይገቡ ዛሬ በመጣው ፍርድ ይዳኙ ነበር፡፡  ምን አልባትም እንደምናስበው ሳይሆን እነዚህ ሰዎች የተሸለ ስብእና ሳይሆራቸው አይቀርም ከወያኔ ነጥሎ በቀላል ወንጀል ተጠያቂ መሆን ያበቃቸው፤፡ ለመሆኑ ግን መቀሌ ሄደዋል የተባለው እነ አዲሱ ለገሰ ገነት ዘውዴ ምናምን የመሳሰሉት የት ናቸው? ነው ውሸት ነበር መቀሌ ሄደዋል የተባለው፡፡  ለማንኛውም የመከላከያው የታማጆር ሹም እንዲህ ያለ ነገር በዘራችሁ አያድርስባችሁ ያሉት በእርግጥም ከልባቸውና ሁኔታው እጅግ አሳዛኝ ስለሆነባቸው ነበር፡፡ ብዙ ሰው ብርሁኑ ይሄን ሲናገሩ ሲስቅ ተመልክቻለሁ፡፡ ታላቅ አባባልና መልዕክት ነበር፡፡ ሁኔታውን ላስተዋለ እጅግ የሚያሳዝን እንጂ የሚያስቅም አደለምና፡፡

በውጭ ያሉ ወያኔዎች (ትግሬ በሙሉ ብል ይሻለኛል) እብድ ሆነዋል፡፡ መቼም ሴራና ውሸትና ተንኮል እንጂ ምንም እውቀት ስለሌላቸው  በቀጣይ በእነሱም እየመጣ እንደሆነ እያስተዋሉ አይመስለኝም፡፡ በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን የወያኔ ደጋፊዎች የባንዳ የልጅ ልጆች ስለ ኢትዮጵያ የሚያገባቸው እንደሌለ ልትነግሯቸው ይገባል፡፡  አያቶቻቸው ለጣሊያን ባንዳ ሆነው መስራት ሳያስነሳቸው ዛሬ የእነዛ ዘሮች ጣሊያን መቋቋም ያልቻላትን ኢትዮጵያን እኛንው መስለው 27 ዓመት ለመግዛት እድል አግኝተዋል፡፡ ከእነዚህ ዘሮች አንድም ጀግና እንዳልወጣ አስተውሉ፡፡ አሉላም ሆነ ዮሐንስ የተንቤን ተወላጆች እንጂ ከአደዋ አደሉም፡፡ ተንቤን በወያኔ ዛሬም ድረስ እንዴት እንደሚታይ እናውቃለን፡፡ የሚገርመው ድሮም በአስራ ሰባት ኣመት የወንበዴነት ጊዜያቸው ይዘውት የነበረውን ቆላ ተንቤን ዛሬም መቀበሪያቸው እንዲሆን ሆነ፡፡ ያ ቦታ የእነሲዬ አብርሀ ዘመዶች ቦታ ነው ይባላል፡፡ ቦታውን እኔ ከሞላ ጎደል አውቀዋለሁ፡፡ ከአብ አዲ ከተማ ምዕራብ የሚገኝ ነው፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

4 Comments

 1. ድንቅ ነው ተወልደ እንዳለው በታሪክ ታዝለው የተማረኩ ሽፍታ አቦይ ስብሀት ብቻ ናቸው ምናልባትም ሚስታቸውም ሳይታዘሉ አይቀሩም ያንን ዋሻ መውጣት ስለማይችሉ። ወዳጃቸው አብይ በገደሉት ዜጋ በዘረፉት ንብረት ሊጠይቃቸው አልፈለገም ነበር እነሱ ጀምረው ፍጻሜው ይሄ ሆነ አሁንም ቢሆን ለአሳዳጊዎቹ ስስ ልብ ስላለው በክብር ያኖራቸዋል። ለሱ የህዝብ ጠላት እስክንድር ነው ስብሀት ነጋንም እንዲህ ያዋረደው ግፉ ተጠራቅሞ ነው የእሱንም ወደፊት እናያለን ።

 2. በወታደራዊ መንግስት እስተዳደር ፖለቲከኞች እና በሲቪሊያን መንግስት አስተዳደር ፖለቲከኞች መሀከል ያለውን የመርህ ልዪነት ለማጥበብ የታሪክ ጠባሳን ማከም ያስፈልጋል።

 3. semere

  እስከ የመናፍስንት ዘመን ወደኋላ ተመልሰን ታሪክ ላለመተረክ ከግርማሜ ንዋይ እና ከመንግስቱ ነዋይ አብዮት ጀምረን እስከ አሁን ድረስ የሀገሪቱን የፖለቲከኞች ታሪክ ብንገመግም ዘጠኙን የወታደራዊ መርሆች (the nine military principles) እንድ በአንድ ተራ በተራ የሚተገብሩ ፖለቲከኞች እና ዘጠኙን የወታደራዊ መርሆች (the nine military principles) የማይተገብሩ ጨርሶውንም የማያውቁ ፖለቲከኞች ብለን ለሁለት መክፈል እንችላለን። አደርባይ ወላዋይ መርህ የሌላቸውን “ፖለቲከኞችን” ከቁጥር እስካልቆጠርናቸው ድረስ።

  ዘጠኙን የወታደራዊ መርህ የሚከተሉ ፖለቲከኞች ግባቸው ምን እንደሆነ ማወቅ ቢከብድም መርሁን የሚተገብሩበት አክያሄድ ሀገሪትዋን የሴራ ፖለቲከኛ እብጠልጥልዋት አሁን ለምንገኝበት ውጥንቅጥ አብቅቶናል። ውጥንቅጡን አላየንም አልሰማንም ብለን ለማለፍ ሶስት አመት ሙሉ ተሞከረ፡ አልተሳካልንም። ውጥንቅጡ እጅ እግር አውጥቶ ሀገሪቷን እያዳረሰ ነው።
  ጥያቄ፡ታድያ መፍትሄው ምንድን ነው?
  መልስ፡ብሔራዊ ንግግር እና መግባባት
  ጥያቄ፡ማን ተነጋግሮ ይግባባ ?
  መልስ፡ፖለቲከኞች
  ጥያቄ፡ምንድን ነው ምክንያቱ ፖለቲከኛዎቹ እና ፓርቲዎችም እንዲህ የበዙበት ጫጫታ የሆነበት ንግግሩ
  መልስ፡ሰሜን እዝን የሚገድል ርዕሰ መስተዳድር እና ቢጤዎቹ ሥልጣን በያዙበት ሀገር ፖለቲከኞቹም ፣ ፓርቲዎችም እና ጫጫታውም ባይበዛ ነበር እንጂ የሚገርመን መብዛታቸው አይገርምም።
  ጥያቄ፡ ጁንታ ፈርሶ ተይዞ ምነው ውጥንቅጡ አላባራም?
  መልስ፡ ጁንታ tplf ሳይመሰረት በፊት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የዘለቀው የወታደራዊ አስተዳደራዊ መርህ ተከታዮች እና የሲቪሊያን አስተድደራዊ መርህ አለመግባባት ስላላባራ።
  ጥያቄ፡ ምነው እስከአሁን አለመግባባቱ አላባራ?
  መልስ፡ የአመግባባቱ ሰለባዎች ቁስላቸው ማመርቀዙ ሳይቆም ሌላም ቁስል እየተጨመረባቸው በውጥንቅጥ ውስጥ ስለሚገኙ አሁንም።
  ጥያቄ፡ምን በጀ ታድያ?
  መልስ፡ቁስሉን ማከም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.