የዘሐበሻ የዕለቱ ዜና እና የኢትዮጵዊያን አመለካከት

ስዩም ተከቧል! – በ አርአያ ተስፋማሪያም

4 mins read
1
የድል ዜና!
ገርአልታ ተብሎ በሚጠራውና ከመቀሌ ድንበር 18 ኪ/ሜትር፣ ከመቀሌ ከተማ ደግሞ በግምት ከ 35 እስከ 40 ኪ/ሜትር በምትገኘው ስፍራ በነጭ ውሸታምነት የሚታወቀው ስዩም መስፍን ተደብቆ እንደሚገኝ ሲታወቅ የመከላከያ ሰራዊት ስዩም የመሸገበትን ቦታ ከቦ እንደሚገኝ ከትግራይ የተገኘው ጥቆማ ያመለክታል። ኦፕሬሽኑ እንደተጀመረ የጠቆሙት ምንጮች ዛሬ ምሽት ወይም ነገ ጠዋት ድረስ እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ተከዜ ከታየዘው ስብሃት ነጋና ሚስቱ ኮ/ል ፀአዱ እንዲሁም የጁንታው አባላት በተጨማሪ ከፍተኛ አመራሮች በመከላከያ ኮማንድ ሃይል እርምጃ እንደተወሰደባቸው ታውቋል። ለጊዜው ስማቸውን በይደር ላቆየውና ነገ ጠዋት በETV – VOT ቻናል ከረፋዱ አምስት ሰአት ጀምሮ የቀጥታ ስርጭት ቃለምልልስ ስለሚኖረኝ ዝርዝር መረጃዎችን ይዤ ስለምቀርብ እንድትከታተሉ እጠቁማለሁ።
ኢትዮጵያንና ትግራይን በራሱ ቡድን ቁጥጥር ስር አድርጎ በራሥነት ይሰራ የነበረው ስብሐት ነጋ መያዙን በማስመልከት የመቀሌ ኗሪና መከላከያ በጋራ ደስታቸውን ለመግለጽ ነው።”
Wonde Berhanu Kabaw

1 Comment

  1. ወያኔ ማለት ሰው በላ አረመኔ ማለት ነው። እስቲ ጭርቅህን ጥለህ ካላበድክ በስተቀር በዘር ፓለቲካ ሰክረህ እንዴት ከአሜሪካ ወጥተህ በትግራይ ገደል ወድቀህ ትሞታለህ? ይገርማል። እኔን የማንልበት ነገር እኮ ሆነብን አቦ። መብረቃዊ ጥቃቱ በራሳቸው ላይ ወድቆ ይኸው በሰፈሩት መስፈሪያ መሰፈር አይቀርም እንደ ቅጠል እየረገፉ ነው። የትግራይ ልጆች ደም ለፍትህ ይጣራል። በሃገሪቱ በተለያዪ ስፍራዎች የፈጸሙት በደል ወዪ ላንተም ቀን አለ ብሎ ነበር። አያቴ ያልሞተ ሰው ብዙ ያያል ይሉ ነበር። ምነው እነ ፕ/ መስፍን፤ እነ ፕ/አስራት እና ሌሎችም የሃገሪቱ የቁርጥ ቀን ልጆች የወያኔን የሮም አወዳደቅ አይተው ቢሆን? እንዲህ ነው የሃገራችን ፓለቲካ እንደ ሰካራም ሰው ዚግዛግ መጓዝ። ከዘመናት በፊት አንድ የጊዜው አለቃ ገቢያ ላይ የአንድን ወንድም ኢዲዪ ነህ ብሎ ለማንጠልጠል ቆሞ ይደሰኩራል። በንግግሩ ማብቂያ ላይ እኔ አንተን ገድዬ ብከተልህ ደስ ይለኛል በማለት ያናፋል። ተሰብሳቢውም ለመኖር ያጨበጭባል በዚህ መካከል ሰውዬው ተጎትቶ በርሚል መሳይ ነገር ላይ ይወጣና የምትናገረው ነገር አለህ ወይ ሲባል ሞት ለአንተም አይቀርልህም በግፍ ገድለኸኝ ተከተለኛለህ ይለዋል። ገመድ ከአንገቱ ገብቶ በርሚል መሳይ ነገሩ ተገፍትሮ ሰውየው ተንጠልጥሎ ይታያል። ድንገት ሳይታሰብ የጥይት እሩምታ ይሰማል። ያ በጉራ ተነፍቶ አንተን ከገደልኩ በህዋላ ብከተልህ ደስ ይለኛል ያለው ባለስልጣን ጥይት በግንባሩ ገብታ ከተገፈተረው በርሚል ስር ወድቋል። ጫጫታ ኡኡታ ሆነ። ገዳይና ተገዳይ በደቂቃዎች ልዪነት አለፉ። የባለስልጣኑ ገዳይ የተሰቃይ ታናሽ ወንድም ነበር። እንዲህ ነው ፍትህ።
    በሃገራችን ታሪክ እንደ ወያኔ ያለ ድርቡሽ ተፈጥሮ አያውቅም። እናቶች እያለቀሱ ደ/ጽዩንን ሲለምኑት ለሰላም እንባቸውን እና ልመናቸውን ረገጠው። ይህ አልበቃ ብሎ ሁለት አመት ደግሶ እራሱ ያቆመውን ሰራዊት በዘር ከፍሎ ከውጭና ከውስጥ መታው። እንዴት ባለ የሂሳብ ስሌት ነበር ወደ ሚኒሊክ ቤ/መንግሥት እንደገና ሊመለሱ ያቀድት። በትግራይ ህዝብ ላይ 45 አመት፤ በኢትዪጵያ ህዝብ ላይ ለ 27 አመት የፈጸሙት በደል እንዴት አይታያቸውም? አልሆነ እንጂ እንዳሉት ተሳክቶ ቢሆን ኑሮ በጭራሽ ህዝቡ ያልቃል እንጂ ጎንድርና ጎጃምን አልፈው አዲስ አበባ የሚገቡበት ቅዥት ካልሆነ በስተቀር የማይታሰብ ነገር ነው። እኔ ወያኔዎች ሁሉም ቢሞቱ ደስ ይለኛል። ከሰው ተራ የወጡ አረመኔዎችን ናቸውና! ከመካከላቸው አንዳቸውም የሰው ልጅ ስብዕና የላቸውም። ስዪም መስፍንና ጌታቸው ረዳ በውሸት የተጠመቁ ሌቦች ናቸው። በሃገሪቱ ስም አምባሳደር፤ የሰላም አስከባሪ፤ የንግድ ተወካይ፤ ወዘተ እየተባሉ የወጡትና የሰሩት ሁሉ ናዚዎች ናቸው። ምናቸውም አይታመን። በባንክ፤ በመንግሥት መ/ቤቶች፤ በአክሲዪን ድርጅቶች፤ በእርሻ ልማት የሰሩት ዝርፊያና ግፍ ይህ ነው ብሎ ለመተመን ይከብዳል። አሁን ከአሜሪካ ሂዳ ገደል ገብታ ሞተች የተባለችው እነርሱ ገፍትረዋት ይሆናል፡ ቧሏንስ እነርሱ አይደል እንዴ የገደሉት። ገድለው ሃውልት ማቆምና የተቋማትን ስያሜ በሙታን መሰየም ከማጭበርበሪያ መንገዳቸው አንድ ነው። ሆለታ (ገነት) ጦር ት/ቤት ወደ ቀደመው ስሙ ይመለስ። ወያኔ ታሪኩ ይጥፋ። ገና ተራፊው ካድሬ በትግራይ እየተፈላለገ ይባላል። ስንት የትግራይ አባቶችና እናቶች መከራቸውን ተሸክመው ኑረዋል። አሁን ጸሃይ ወጥታለች። ደም አፍሳሾች፤ አፋኞች፤ እየተፈለጉ ጉድጓድ መግባት አለባቸው። የትግራይ ህዝብ ይበቀላል። ማን ማን መሆኑን ያውቃል። በውጭ ሃገር ያሉትንም የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ ጠበቃ በማቆም በደላቸውን ለዓለም ህዝብ በጽሁፍና በቪዲዮ የተደገፈ አድርጎ ካቀረበ ጋማቸውን ተይዘው (ዜጋ ከሆኑ ዜግነታቸው ሁሉ ተቀምቶ) ወደ ሃገር ገብተው ሊዳኙ ይገባል። ስንቶች አሉ አሁን ውጭ ሆነ የሙታን ጡሩንባ የሚነፉ። አቦይ ስብሃት አፋፍ ላይ ደርሷል እያሉ ወሬ የሚያናፍሱ? የእናንተም ቀናችሁ ቅርብ ነው። የዘራፊና የሌባ ልጅ ሁልጊዜም እንዲህ ነው። በባዶ ሜዳ ላይ ድል በድል ሆንን ማለት። ነገርን አርቆ በማየት እውነቱን መረዳት አለመቻል። የእውራን ስብስብ፡፤ በትግራይ ህዝብ ስም ነጋጅ! ገና ብዙ እንሰማለን! እንሰንብት። በቃኝ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.