የዘሐበሻ የዕለቱ ዜና እና የኢትዮጵዊያን አመለካከት

ዕዉነት በነጻ አዉጭነት የተደራጁ ፖለቲካ ተቋማት በህዝብ ዉሳኔ የሚገዙ ይሆናሉ ? – ማላጂ

15 mins read

የ፭ ሽ ዘመን የነጻነት ታሪክ ባላት አገር በነጻነት ትግል ስም ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በህዝብ እና በአገር መስዋዕትነት በተገኘ ለዉጥ በስደት የነበሩት ሲገቡ ጊዜ ደርሶ  ለሩብ ምዕተ ዓመት ከነጻ አዉጭ ትግል ወደ አዉራ ድርጅት እና መንግስት መንበር ላይ የነበሩት የቀደመዉን የሥልጣን መዋጃ ፈቃድ ከነበረበት አንስተዉ ለዳግም ነጻነት ከመሀል አገር አፈግፍገዋል ይህም ሁለተኛ ዓመት አሳልፈዋል፡፡

ሆኖም በ1983 ዓ.ም. በህዝብ ትግል በተገኘ ለዉጥ ሁለቱ ነጻ አዉጭ ግንባር ድርጅቶች( አነግ እና ትህነግ) የነበራቸዉ ጋብቻ በአንድ ሰሞን ተፈፅሞ በዚያዉ ሰሞን ተለያይተዋል፡፡

ቀጥሎም ኦነግ ወደ መጣበት ሲገፋ ትህነግ ተደላድሏል ሆኖም ተራዉ ሲደርስ መጋቢት 24፣2010 ዓ.ም ዳግም በ1984 ዓ.ም. የተሰደደዉን ቤት ለዕንቦሳ ብሎ ትህነግን ወደ ነበረበት መልሷል፡፡

ይህ ሁላ የሆነዉ ታሪክ ራሱን ይደግማል በሚለዉ የቀደመ አበባል ለመግለፅ እንጅ ከህዝብ የዘመናት መሪር ትግል ዉጭ የትኛዉም አካል በሃሳብ ልዕልናም ሆነ በኃይል አልነበረም ፡፡

እዚህ ጋ ልብ ሊባል የሚገባዉ የነጻነት ታጋይ የሚሉት ድርጅቶች ድካማቸዉ ለአገር እና ህዝብ ሳይሆን ለራሳቸዉ የማያባራ የስልጣን ጥም ህዝብን ከህዝብ ጠላት እና ወዳጅ በማድረግ ፍረጃ የዘመናት ስልታቸዉ ዛሬም በቆመበት መገኘቱ ነዉ ፡፡

የነርሱ በህዝባዊነት ሆነ በብሄራዊ ስሜት አለመገዛት ሳይሆን ጥያቄዉ ሲታሰር ወደ እኔ ሲፈታ ወደርዕርሱ መሆናቸዉ እና በግልፅ ለህዝብ አለመቅረብ ባህሪያቸዉ እና የዘመናት ድርጊታቸዉ ከቀድመ ስልልጣን አሁን አስከሚገኙበት ደረጃ ያለዉ ታሪካዊ ሂደት ሲታይ ለመጭዉ ምርጫ እንዴት ሊመጥኑ እንደሚችሉ ሊያስረዳ የሚችል አካል አለመኖር ሌላዉ ወቅታዊ ጥያቄ ነዉ ፡፡

በነጻ አገር እና ህዝብ ምድር ሆነን ጨቋኝ እና ተጨቋኝ ህዝብ እየተፈረጀ  በቀቢፀ ተስፋ ጥላቻ እና በማይጨበጥ የትየለሌ ፍላጎት ለራስ ወገን ፣ ለህዝብ እና አገር አለመጨነቅ የሚያሳየዉ በስልጣን ላይ የነበር ከስልጣን መንበር ሲገፈተር ነጻ አዉጭ ወደ ስልጣን ማማ ሲወጣ መከራ አምጭ የሚሆንበት አግባብ በመንግስት እና ህዝብ አለመታሰቡ የሚያሳየን ዛሬም ከትናንት ሳንማር ለነገ የዕድገት ዕንቅፋት እና እሾክ  እየደረደርን እና እየዘራን መሆኑን አዉቀን እንደ ህዝብ አሁን ልናስብበት ይገባል ፡፡

በምርጫ ሂደትም በአገራችን  በነጻ አዉጭነት  ተመዝግበዉ የሚገኙ ሶስት የፖለቲካ ተቋማት መኖር ከነበራቸዉ የቀደመ ምግባር እና ተግባር የተስተካከለ ሆነ የተለወጠ ነገር አለመኖሩ እየታወቀ እና ዛሬም በህዝብ እና በአገር ላይ ለሚታይ ተደጋጋሚ የሠለም እና በደህንነት የመኖር ስጋት ምክነያት መሆናቸዉ እየታየ ዘላቂ እና ወጥ አገራዊ መፍትሄ ባልተሰጠበት ሁኔታ በሽፍንፍን መተላለፍ ዉሎ ሲያድር ሊያስከትል የሚችለዉን መጠላለፍ ሠፊዉ ህዝብ ፣ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን እና መንግስት ሊያስቡበት ይገባል ባይ ነን ፡፡

እዉነተኛ ህዝብ እና መንግስት ካከፉት እና አስከፊ ክስተቶች መማር ነዉ ፤ አበዉ “ጥንቃቄን ከድለ ቢስ ይማሯል ” እንዲሉ ፡፡

የቀደመዉ አንሶ ዛሬም በዕሳት የሚጫወቱ ነገ ስልጣን ላይ የመዉጣት ዕድል ቢገጥማቸዉ ምን ሊሆኑ እና ሊያደርጉ እንደሚችሉ እና ጠላት እና ወዳጅ ብለዉ ለሚመለከቱት ህዝብ ዉሳኔ ሊገዙ ስለመቻል አለመቻል ስናስብ እና ስንገምት ለዘመናት ያልተፈጠረ ስብዕና በምርጫ ሊቀየር እንደማይችል መገመት ጠንቋይ መቀለብን ወይም ነብይ መሆንን አይጠይቅም ፡፡ በአጭሩ ሠዉ መሆን እና ለራስ በጎ ማሰብ ላለዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚቻል ዕይታ ነዉ ፡፡

ለሁላችን የሚበጀን ለሁላችን በመትሆን አገር ሳይቃጠል በቅጠል ካልሆነ  አንዱ ዕሳት ሲለኩስ ሌላዉ ሲቃጠል በዓመድ መረማመድ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ሊቆም ቢችል ከወል ጥፋት ወደ ጋራ ዕድገት እና ብልፅግና የመዳረስ ዕድል በዕጃችን ነዉ ፡፡  

                                                            ማላጂ

                                                                                                                                     

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.