ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.
ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ
“ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን” ብለው አንድነታችንን የሚያጠናክር ንግግር ሲናገሩ የኢትዮጵያኒዝምን ፍልስፍና ጥቅም በሚገባ እንደ ገለጹት ተረድተናል። ቀጥለውም ኢትዮጵያን ከኢትዮጵያ መውሰድ ይቻላል! ነገር ግን ከኢትዮጵያዊ ልብ ኢትዮጵያ ዘላለም አትወጣም ትኖራለች! ብለው የኢትዮጵያኒዝምን ፍልስፍና ጥቅም ደግመው አጉልተውታል።