ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይናው ታዩዋን ከተማ የሳተላይት ማስወንጨፊያ ማዕከል ወደ ህዋ ያስወነጨፈቻትን ˝ኢት አር ኤስ ኤስ 1˝ በይፋ ከቻይና ተረከበች።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ሳይተላይቷን ማስወንጨፏ የሚታወስ ነው።
የሳተላይቷ ይፋዊ ርክክብ ቀደም ብሎ በሁለቱ ሀገራት የዘርፉ መስሪያ ቤቶች በኩል ለማከናወን ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም የኮሮና ቫይረስ በፈጠረው የጉዞ መስተጓጎል ምክንያት ሳይከናወን መቆየቱ ተጠቁሟል።
በዚህም በሁለቱ ወገን በተደረሰ ስምምነት በቻይና ኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ እንዲረከቡ በተወሰነው መሰረት በትናትናው ዕለት በቻይና ስፔስ ቴክኖሎጂ አካዳሚ በተካሄደ ስነ-ስርዓት ርክክቡ ተፈፅሟል።
ኤፍ.ቢ.ሲ